1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፤ የተቃዉሞ ሠልፍና እንቅፋቱ

ሰኞ፣ መስከረም 20 2006

የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሳይሆን በፈረንሳይኛ፥ በእንግሊዝኛ ወይም በሌላ የአዉሮጳ ቋንቋ ለሚዘግቡት አልጠፉም።

https://p.dw.com/p/19rvJ
ምስል DW

መፈክሩ ባደባባይ ተነገበ፥ ተቀነቀነም።አዲስ አበባ ትናንት።ጩኸቱም ቀጠለ።ሰሚ-ያገኝ ይሆን?


«የታገተ ወይም በቁጥጥር ሥር የዋለ አንድም ሰዉ አላዉቅም።» አቶ ሪድዋን ሁሴን የኢትዮጵያ የኮሚንኬሽን ጉዳይ ሚንስትር ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ትናንት እንደነገሩት።


አቶ ግርማ ሰይፉ የምክር ቤት እንደራሴና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር።የትናንቱ የአዲስ አበባ የተቃዉሞ ሠልፍ መነሻ፥ የመንግሥት አፀፋ ማጣቃሻ፥ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እዉነትና ሒደት መድረሻችን ነዉ-ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
መግባባት ቢቀር ለመቀራረብ ከቁጥር የቀለለ ነገር በርግጥ የለም።ትናንት ለተቃዉሞ ሠልፍ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ ቁጥር ሥንትነት ግን የሰልፉ አደራጆችንና የመንግሥትን ሹማምንት ከሚገመተዉ በላይ ነዉ-ያራራቀዉ።

ይላሉ አቶ ግርማ ሰይፉ። ሠልፉን ከጠሩና ካደራጁት ሰላሳ ሰወስት ፓርቲዎች የዋነኛዉ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ምክትል ሊቀመንበርና የምክር ቤት እንደራሴ ናቸዉ።ጉዳዩ የሚመለከታቸዉን የመንግሥት ባለሥልጣናትን ቀጥተኛ መልስ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ሞከርን።አሰልቺ ሙከራ።የገሚሶቹ ሥልክ አይነሳም።የሌሎቹ ዝግ ነዉ።ሌሎቹ ቢሯቸዉ የሉም ተባለ።የተለመደ መልስ።

የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሳይሆን በፈረንሳይኛ፥ በእንግሊዝኛ ወይም በሌላ የአዉሮጳ ቋንቋ ለሚዘግቡት አልጠፉም።

እንደራሴ ግርማ ሥለ-ሠልፈኛዉ ቁጥር ባማርኛ ከሰማንያ ሺሕ እስከ መቶ ሺሕ ያሉትን የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሚንስትር አቶ ሪድዋን ሁሴይን «ጥቂት መቶዎች» ማለታቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ በእንግሊዝኛ ዘገባዉ ጠቅሶታል።

እንደ ቁጥሩ ሁሉ-የሠልፉ ሥፍራም አሳካሪ ነበር።አብዮት አደባባይ ወይም መስቀል አደባባይ፥ጃን ሜዳ፥ ወይስ በየሥፍራዉ።ግራ ነዉ።ሠልፍ የመጥራት ማደራጀቱ ሒደት፥አደራጅ ቀስቃሾች የገጠማቸዉ ፈተና ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እንደሚሉት ከግራ ከማጋባትም ከባድ ፈተና ነበር።ሠልፉን ከጠሩት ፓርቲዎች አንዱ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዝዳት አቶ አበባዉ መሐሪ እንደሚሉት ትናንት የሆነዉ ከእስከ ትናንቱ ሁሉ የከፋ ነዉ።

አቶ ግርማ የምክር ቤት እንደራሴ ናቸዉ።የትናንቱን ሠልፍ ሲጠሩና ሲያደራጁ ግን የእንደራሴነታቸዉ መብት በፀጥታ መኪና ከመታጀብ፥ ከማስፈራራትና በቁጥጥር ሥር ከመዋል አላዳናቸዉም።

የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትሩ አቶ ሪድዋን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደጠቀሰዉ በቁጥጥር የዋለ ሰዉ መኖሩን አያዉቁም።አቶ ግርማ እንደሚሉት ግን ራሳቸዉን፥ የፓርቲያቸዉ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ የፓርቲዉ ባለሥልጣናትና የሠልፉ አደራጆች ባለፈዉ አርብ በቁጥጥር ስር ዉለዉ ነበር።
----
ሠልፈኛዉም አለዉ።ዉሸት ሠለቸን።
----
አቶ አበባዉ ገለጡት።
---
ፖለቲከኛ፥ የፖለቲካ ተንታኝ፥ ሐያሲና ደራሲ አቶ አስራት አብረሐ እንደሚሉት ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ለአደባባይ ሠልፍ እዉቅና እየሰጠ በገቢር ሲከለክል፥ ሰዉ እየወነጀለ ሲያስር፥ ደግሞ ሲለቅ የትናንቱ የመጀመሪያዉ አይደለም።
----
«የኢሕዴግ ቤተ-ሙከራ»።የገዢዉን ፓርቲ እርምጃ አቶ ግርማ ኢሕአዴግ የትጥቅ ትግልን ለመረጡ ወገኖች አባላት ከመመልመል የሚቆጠር ይቆጠር ይሉታል።
------
የአቶ አበባዉም አስተያየት ምሬት አዘል ነበር።
-----
ሠላማዊዉ ትግሉ እንዴት መቀጠል አለበት? አቶ አስራት ተቃዋሚዎች አዳዲስ ሥልት መቀየስ፥ አደረጃጃት ላይ ብዙ መሥራት፥ ከሁሉም በላይ መቀራረብ አለባቸዉ ባይ ናቸዉ።

የመኢአዱ ፕሬዝዳት አቶ አበባዉ መሐሪ እንደሚሉት ፓርቲያቸዉ ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ተባብሮ መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።

አቶ ግርማም አንድነት ከዚሕም አልፎ ተባብሮ መሥራት በአምስት-ዓመት መርሑ እንደ ግብ አስቀምጦታል።

የትናንቱ የተቃዉሞ ሠልፍ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ መሪነት፥ በመኢአድ ተባባሪነት ሁለቱን ጨምሮ በሰላሳ-ሰወስቱም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር መደረጉ ተቃዋሚዎች የጋራ ጠንካራ ሐይል ለመፍጠር ያላቸዉን ፍላጎት ጅምሩንም ጠቋሚ ነዉ-ባዮች አሉ።ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚፈለገዉን ነፃነት፥ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት ግን የፖለቲካ ተንታኝ አስራት አብረሐም እንደሚሉት የተቃዋሚዎች ትብብር ብቻዉን በቂ አይደለም።ከ«አሳፋሪ ፖለቲካ» የመዉጣቱ ተስፋም አቶ አሥራት እንዳሉት ቢያንስ ባጭር ጊዜ በግልፅ አይታይም።ነጋሽ መሐመድ ነኝ።ለዛሬዉ በቃን።

UDJ - Demonstration der Oppositionspartei in Äthiopien
ምስል DW/Y.G. Egziabher
UDJ - Demonstration der Oppositionspartei in Äthiopien
ምስል DW/Y.G. Egziabher
Bildergalerie Demonstration Oppositionspartei UDJ in Äthiopien
ምስል DW
Bildergalerie Demonstration Oppositionspartei UDJ in Äthiopien
ምስል DW

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ