1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦምብ ፍንዳታዎቹ አንድምታ

ሐሙስ፣ ጥር 4 2009

የአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች የሆኑት ባሕር ዳር እና ጎንደር ተከታታይ የቦምብ ጥቃት አስተናግደዋል።

https://p.dw.com/p/2Vi4L
Fasil Schloss Gonder Äthiopien
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

Q & A (Gonder Bombenanschlag Analysis) - MP3-Stereo

የአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች የሆኑት ባሕር ዳር እና ጎንደር ተከታታይ የቦምብ ጥቃት አስተናግደዋል። ጥር ሁለት ቀን 2009 ዓ.ም በጎንደር ማራኪ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 18 በሚገኘው ኢንታሶል አነስተኛ ሆቴል ላይ በተፈጸመው ጥቃት የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል። ታኅሳስ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መፈጸሙ አይዘነጋም። እስካሁን ድረስ ከሁለቱ ፍንዳታዎች ጀርባ ማን እንዳለ የሚታወቅ ነገር የለም። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወገን ካለመኖሩም ባሻገር የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ ቦምብ ፍንዳታዎቹ የሰጠው ተጨማሪ መረጃ የለም። ሁለቱ ከተሞች ከወራት በፊት ፖለቲካዊ ተቃውሞእና ኹከት ከተከሰተባቸው መካከል ይገኙበታል። ሁለቱ ቦምብ ፍንዳታዎች ከተቃውሞ እና ኹከቱ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር ይኖር ይሆን?  በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ስልታዊ ጥናት ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አቶ አበበ አይነቴን  አነጋግሪያቸው ነበር። 
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ