1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝን ለዉጭ ገበያ

ዓርብ፣ መስከረም 21 2008

አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን ሀገሪቱ በሦስትና አምስት ዓመት ጊዜ ዉስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር መግለፃቸዉን አሶስየትድ ፕረስ ዘገበ።

https://p.dw.com/p/1Ghvs
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን ሀገሪቱ በሦስትና አምስት ዓመት ጊዜ ዉስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር መግለፃቸዉን አሶስየትድ ፕረስ ዘገበ። ባለስልጣኑ እቅዱን የገለፁት ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መገኘቱ ይፋ ከሆነ በኋላ መሆኑን ዘገባዉ አክሎ ገልጿል። የኢትዮጵያ የማዕድን ሚኒስትር አቶ ቶሎሳ ሻጊን ዋቢ በማድረግ የዜና ምንጩ እንደዘገበዉ ኢትዮጵያ ይህን የተፈጥሮ ጋዝ ለዉጭ ገበያ በማቅረብ በዓመት አንድ ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል። እንደዘገባዉ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 4,7 ትሪሊዮን ኩቢክ ጫማ ላይ ያለዉን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የቻይና ኩባንያ እንዳገኘ በመግለፅ፤ የሀገሪቱ ዉስጥ የጋዝ ፍላጎት ከተሟላ በኋላ ለዉጭ ገበያ መቅረብ እንደሚጀምር አመልክተዋል። የተፈጥሮ ጋዙ በተገኘበት አካባቢም የደሕንነት ጥበቃዉ መጠናከሩንም አስታዉቀዋል። ይህ የሆነዉም በጎርጎረሳዊዉ 2007 ዓ,ም የ65 ኢትዮጵያዉያን እና 9 ቻይናዉያን የነዳጅ ፍለጋ ሠራተኞች ላይ የደረሰዉ አይነት ጥቃት እንዳይከተል በማሰብ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር አቶ ቶሎሳ ሻጊ መግለፃቸዉ አሶስየትድ ፕሪስ ዘግቦአል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ