1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የፀጥታዉ ምክር ቤት ፕሬዝደትነት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 25 2009

ለአንድ ወር በሚቆየዉ የፕሬዝደንትነት ሥልጣንኗ ምክር ቤቱ ለአፍሪቃ በተለይም ለምሥራቅ አፍሪቃ ሠላም ትኩረት እንዲሰጥ ለማድረግ ትጥራለች።

https://p.dw.com/p/2j9wg
USA UN-Sicherheitsrat in New York - Sondersitzung zu den Rakektentests in Nordkorea
ምስል Reuters/A. Kelly

(Beri.WDC) Äthiopien-Sicherheitsrat - MP3-Stereo

 ኢትዮጵያ በየወሩ የሚቀያየረዉን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የፕሬዝደንትነት ሥልጣን ነገ ትረከባለች። በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ቃል አቀባይ አቶ ብሩክ መኮንን እንዳሉት ለአንድ ወር በሚቆየዉ የፕሬዝደንትነት ሥልጣንኗ ምክር ቤቱ ለአፍሪቃ በተለይም ለምሥራቅ አፍሪቃ ሠላም ትኩረት እንዲሰጥ ለማድረግ ትጥራለች። የአፍሪቃ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሰባ የሚደረገዉም በኢትዮጵያ የፕሬዝደንትነት ወቅት ነዉ። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ