1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር

እሑድ፣ ሰኔ 4 2009

የደርግን ሥርዓት የተካዉ ህወሀት መራሹ ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበት 26ኛ ዓመት ባለፈዉ ግንቦት ሃያ ተከብሯል። ኤሕአዴግ ሥልጣን እንደያዘ የሕዝቡን የፖለቲካና ማኅበራዊ ችግሮች ለማስወገድ መቁረጡን ገልጾ ነበር።

https://p.dw.com/p/2eQzo
Äthiopien vor der Wahl EPRDF Anhänger in Addis Abeba
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ መሠረታዊ መብቶች መከበራቸዉን የሚደነግገዉን ሕገ መንግሥት ከማጽደቅ አንስቶ፤ በፖለቲካዊም ሆነ በኤኮኖሚዉ ዘርፍ ቀላል የማይባሉ ተግባራት መከናወናቸዉን ብዙዎች ይስማሙበታል። ለዉጦቹ ተስፋ ሰጪ ሆነዉ አለመቀጠላቸዉ ግን ወትሮ ይነሱ የነበሩ የሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ የመድበለ ፓርቲ ምሥረታ፤ የሕግ የበላይነት ወዘተ ጥያቄዎች ዛሬም እንዲያስተጋቡ ምክንያት እንደሆኑም በሰፊዉ ይታመናል። ኢትዮጵያ አሁን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ትገናለች። ሌላስ?   ለ26 ዓመታት በኢህአዴግ የምትተዳደረዉ ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች? ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ አድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ