1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጽያ፣ በጀርመናዊዉ ደራሲ ብዕር

Azeb Tadesseማክሰኞ፣ ነሐሴ 15 1999

የስልጣኔ በር ከፋችዋን ኢትዮጽያ፣ ያላትን የተፈጥሮ ዉበት፣ የተለያየ ብሄር ብሄረሰብ ያቀፈዉ፣ እንግዳ ተቀባይ ህዝብዋን ካነሳን፣ እኛ ትዉልደ ኢትዮጽያዉያን፣ በርግጥም፣ ምድሪቷ፣ የፈጣሪ ጥበብ መሆንዋን እንመሰክርላታለን

https://p.dw.com/p/E0mE
ቆም ብሎ ከርቀት አስተዋዩ ብዙ ነበር
ቆም ብሎ ከርቀት አስተዋዩ ብዙ ነበርምስል Peter Zimmermann

ምዕራባዉያን ጎብኝዎችዋም፣ በአገሪትዋ ተፈጥሮዋዊ ዉበት፣ ባህል፣ ሃይማኖት ወግ፣ እሴት፣ የሚያገኙት ደስታ፣ ከምንም በላይ ነዉ። ምክንያቱም፣ በነሱ አካባቢ፣ ስለኢትዮጽያ የሰሙት፣ ስለ ኢትዮጽያ የነበራቸዉ ግምት፣ ፍጹም አይገጣጠም። ከዝያም ወዲህ ታድያ፣ ስለኢትዮጽያ አንስተዉ አይጠግቡም። ወደ አገራቸዉ ተመልሱ በኳላ ለዘመድ፣ ለጓደኞቻቸዉ፣ ስላዩት ማዉራት ነዉ፣ ስለበሉት ማዉራት ነዉ፣ በርበሪ ሽሮ ብጤም፣ ከኢትዮጽያ ይዘዉ መተዉ እንደሁ፣ ወጥ ብጤ ሰራ አድርገዉ፣ በፈረንጁ ብረት ምጣድ፣ እንጀራም ሞካክረዉ፣ ወግ ይይዛሉ። ታድያ ወጉ ላይ ቡና እና፣ የቡና ቁርሱ፣ ቆሎ አይቀርም። እዚህ ላይ ታድያ፣ ኢትዮጽያን ጎብኝቶ ያላየዉ፣ ሌላዉ አድማጭ ይህን አይነት ወግ ሲያይ ደስታዉ ከአድማስ ባሻገር ይሆናል። በኢትዮጽያ እጅግ በጣም የተደነቀ ደግሞ፣ ብዕሩን እና ወረቀቱን አገናኝቶ ስለኢትዮጽያ መጻፉን ይጀምራል። ኢትዮጽያን በማየት ስለኢትዮጽያ ለመጻፍ ከተገደዱት መካከል ጀርመናዊዉ Bernd Bierbaum ተጠቃሽ ናቸዉ። ከጽሁፋቸዉ በጥቂቱ ...

“በኢትዮጽያ ያሉትን አስደናቂ አብያተ ክርስታናትን ፈልጎ አግኝቶ መጎብኘት የመታደል አይነት ነዉ ሲል ደራሲዉ በጽሁፉ ወደ ደብረዳሞ ያቀናል። በሎንችና ተሳፍሮ ጎዞዎን ጀምሮ ገዳሙን እስኪያይ ቸኩሏል በሎንችናዉ ዉስጥ አልተመቸዉም። እግሩና እጁ ተሳስሮበት መቼ ገዳሙ ደርሼ ከሎንችና ወርጄ እግሪን አፍታትቼ እያለ በምኞት እንዳለ፣ አይደረስ የለ መድረሱን ይገልጻል። ገዳሙ የሚገኘዉ ቀጥ ብሎ በቆመ ተራራ አናት ላይ መሆኑን ሲገነዘብ እግሩ እና እጁ የበለጠ እንደሚታመም ተረዳዉ። ገዳሙ ለመድረስ ምንም አይነት ደረጃ የለም እንዲያዉ በአንድ ቀጠን ባለች ጠፍር ላይ በመንጠልጠል ነጩን አለት ድንጋይ በግር ጣት ወጥሮ በመያዝ ገዳሙ ለመድረስ በደረት መሳብ ነዉ። እየፈራ ወደ ገዳሙ ለመድረስ ጠፍሩን ይዞ በመንጠልጠል በመሳብ እንደምንም እተራራዉ መሃል ደርሶ ቁልቁል ቢበለከት ተራራዉ ስር ያሉ ሰዎች የወይን ፍሪ ያህል አነሱበት። በጣም ርቆአል፣ ወደ ኳላ መመለስ የለም! ድንገት ቢወድቅ አጥንቱ እንደማይገኝ አወቀዉ! ፈራ! ሁኔታዉን ተራራዉ መሃል ቆመዉ የነበሩ የአካባቢዉ ህጻናት አይተዉ በጣም እንደ ሳቁበት እና እንዳፈረ ይገልጻል። ያ አስለች የሆነዉን የተማረረበትን የሎንችና ጉዞ አመሰገነ። በመጨረሻ አይደረስ የለ ተራራዉ ጫፍ ደረሰ። ይህን ሁሉ መከራ አይቼ ጠፈሩን እየጎተትኩ እየተሳብኩ የደረስኩበት አስፈሪ መንገድ ጠፍሩ የታሰረበትን ችካል ሳይ ደነገጥኩ! ወሸል ብሎ ከመታሰሩ፣ ችካሉ ሊነቀል አንድ ሃሙስ የቀረዉ ይመስላል! የጠፍሩን ጫፍ የያዙት ሰዉ ደግሞ አቅም የሌላቸዉ ሽማግሌ! ተአምር አልኩ! ገረመኝ! ፈራሁ ብዙ ነገር በሃሳቤ መጣ፣ ወደ ደብሩ ወደ ገዳሙ ገባ ስል ግን ሌላ አለም! የደስታ የዉበት የስልጣኔ ገጽ! ያ ሁሉ ድካሜ ጠፋ! ጉልበቴ ታደሰ.....”

ቢርባዉም ኢትዮጽያን ለመጎብኘት እንዲት መረጡ? ጀርመናዊዉን ጸሃፊ ኢትዮጽያ ከተሰኘዉ መጻህፋቸዉ ጋር ያድምጡ