1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢንዶኔዢያ፦በ1 ቤተሰብ አባላት ጥቃት በርካቶች ሞቱ

እሑድ፣ ግንቦት 5 2010

ሁለት ልጆችን ጨምሮ ስድስት አባላት ያሉት አንድ ቤተሰብ ኢንዶኔዥያ ውስጥ በሚገኙ በሦስት አብያተ ክርስቲያን አስከፊ የተባለ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት መፈጸሙን ፖሊስ አስታወቀ። ሱራባያ በተባለችው ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች እና ስድስት አጥፍቶ ጠፊዎች ተገድለዋል። 41 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/2xeO5
Selbstmordanschlag in Surabaya Indonesien
ምስል Reuters/Antara Foto/M. R. Hidayat

ሁለት ልጆችን ጨምሮ ስድስት አባላት ያሉት አንድ ቤተሰብ ኢንዶኔዥያ ውስጥ በሚገኙ በሦስት አብያተ ክርስቲያን አስከፊ የተባለ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት መፈጸሙን ፖሊስ አስታወቀ። ሱራባያ በተባለችው ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች እና ስድስቱ አጥፍቶ ጠፊዎች ተገድለዋል። 41 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የአገሪቱ ፖሊስ አዛዥ ቲቶ ካርናቪያን እንዳሉት አባትየው በመኪና በተጠመደ ቦምብ፣ እድሜያቸው 18 እና 16 የሆነ ሁለት ልጆች በሞተር ሳይክል ጥቃቱን ፈፅመዋል። እናት ዕድሜያቸው 12 እና 9 ከሆነ ልጆቻቸው ጋር ሆነው ሌላ ጥቃት ፈፅመዋል። ካርናቫያን እንዳሉት ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከሶርያ ወደ ኢንዶኔዥያ የተመለሱት በቅርቡ ነበር። ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ታጣቂ አማቅ በተባለ ልሳኑ በኩል ኃላፊነት ወስዷል። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን ስለፈጸመው ቤተሰብም ሆነ ስለ ልጆቹ ያለው ነገር የለም። 

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ