1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢንዶኔዥያ-የሱናሚ መቅሰፍት አስረኛ ዓመት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 17 2007

የዛሬ አስር ዓመት በደረሰዉ ከፍተኛ የባሕር ነዉጥ ወይም ሱናሚ የሞቱትን ሰዎች ፤ በሺህ የሚቆጠሩ የሟቾች ዘመድ ወዳጆች በህንድ ዉቅያኖስ ዳርቻ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች አስበዉ ዋሉ።

https://p.dw.com/p/1EAR3
Zehn Jahre nach Tsunami in Banda Aceh Indonesien
ምስል Getty Images/U. Ifansasti

የዛሬ አስር ዓመት የጎሮጎሮሳዉያኑ ገና ሌሊት ከኢንዶኔዥያ እስከ ሶማሊያ ድረስ የሕንድ ዉቅያኖስን የሚዋሰኑ አስራ-አራት ሃገራትን የመታዉ ሱናሚ ከ230 ሺህ በላይ ሕዝብ ፈጅቷል። የበርካታ ሃገራትን የባሕር ዳርቻ ከተሞችን ባወደመዉ የባሕር ነዉጥ ወይም ሱናሚ ያለቁት ሰዎች አስረኛ ሙት ዓመት ትናንት ባንዳ-አቼ ኢንዶኔዢያ ዉስጥ በልዩ ሥርዓት ታሰቦ ዉሎዋል። በሚሊዮን የሚቆጠር አፈናቅሏል። በብዙ ቢሊዮን የሚገመት ሃብት ንብረት አዉድሟል። በአዳጋዉ ከሞቱት ሰዎች ከ170 ሺሕ የሚበልጡት በሬክተር መመዘኛ 9,3 የተለካዉ የባሕር ነዉጥ ማዕከል የሆነችዉ የኢንዶኔዢያዋ አቼ ክፍለ-ግዛት ነዋሪዎች ነበሩ። የገናን በዓል በሞቃማይቱ ግዛት ለማክበር ወደዚያዉ የተጓዙ የተለያዩ ሃገራት ሃገር ጎብኚዎችም አልቀዋል። ሙታኑን ለማሰብ ዛሬ ማምሻዉን አቼ ዋና ከተማ ባንዳ በሚገኘዉ ታላቅ መስጊድ ዉስጥ በተደረገዉ ፀሎት ላይ ወዳጅ ዘመድ የሙቱባቸዉ በሺሕ የሚቆጠሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ተካፍለዋል። የባንዳ-አቼዉ ባይቱራሕ መስጊድ ከከባዱ ጥፋት ከተረፉ ጥቂት የከተማዋ ሕንፃዎች አንዱ ነዉ።


በታይላንድም «ካኦ ላክ» በተሰኘዉ የባህር ዳርቻ ላይ ከማዕበሉ የተረፉ ሰዎች ጀርመንኛ ቋንቋ የሚችል ቄስን ይዘዉ ሙታንን አስበዋል። በኢንዶኔዥያ በደረሰዉ የሱናሚ አደጋ 539 ጀርመናዉያን ሰለባ መሆናቸዉ ይታወቃል። በስሪላንካም ተጓዦችን የጫነ ባቡር በማዕበሉ ተወስዶ 1600 ተሳፋሪዎች ማለቃቸዉ ይታወቃል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ ከሱናሚ አደጋዉ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተደረገዉን የርዳታ ዝግጁነት አወድሰዋል።


ነጋሽ መሃመድ


አዜብ ታደሰ