1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢዜማ የምርጫው ሒደት የከፋ ነበር አለ

ሐሙስ፣ ሰኔ 17 2013

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)በምርጫው ላይ ታዩ ያላቸውን ከአራት መቶ ስድሳ በላይ ስህተቶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቅረቡን ዐሳወቀ። ኢዜማ የምርጫው የመጨረሻ ውጤት እስኪሰጥ እንደሚጠብቅ ገልጧል።

https://p.dw.com/p/3vVfF
EZEMA Partei Äthiopien Addis Abeba
ምስል Yohannes G/Egziabher/DW

ቅሬታውን ወደ ፍትህ አካላት ይዞ እንደሚኼድም ጠቁሟል

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)በምርጫው ላይ ታዩ ያላቸውን ከአራት መቶ ስድሳ በላይ ስህተቶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቅረቡን ዐሳወቀ። ኢዜማ የምርጫው የመጨረሻ ውጤት እስኪሰጥ እንደሚጠብቅ ገልጧል። በበርካታ ኢዜማ የተወዳደረባቸው ቦታዎች ቅድመ ምርጫ እና  በምርጫ ወቅት አጋጠሙ ያላቸውን  ተግዳሮቶችን በተመለከተ ለምርጫ ቦርድ በተደጋጋሚ በማስረጃ አስደግፎ ማቅረቡንም ጠቅሷል። ምርጫ ቦርድ ቀረቡ በተባሉት ተግዳሮቶች ላይ ውሳኔ የማይሰጥባቸው ከሆነ ወደ ፍትህ አካላት ይዞ እንደሚኼድ በጽሑፍ ንባብ በሰጠው መግለጫ ዐሳውቋል። የፓርቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ችግሩን ለመፍታት ሁሉንም ሕጋዊ ትግል እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ