1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢድ አልፈጥር በአዲስ አበባ እና ቃሊቲ

ረቡዕ፣ ሰኔ 29 2008

1437ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሕዝበ-ሙስሊሙ በታደመበት ዛሬ ጠዋት ተከብሯል። ከስታዲየሙ ውጪም ምዕመናኑ በነቂስ ወጥተው መታደማቸው ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/1JKCc
Äthiopien Addis Abeba Fastenbrechen Eid al-Fitr Gebet
ምስል Reuters

[No title]

ዘንድሮ የኢድ አልፈጥር በዓል ስነሥርዓት በአዲስ አበባ የጀመረው ታዳሚዎች ወደ ስታዲየም ገብተው ሳይጨርሱ ሲሆን፤ የተጠናቀቀውም በጊዜ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኙ ሙስሊም እስረኞችን የመጎብኘት ወይንም የመዘየር ስርዓት ተከናውኗል። በዓልን ብዙዎች በተለያየ መልክ ያከብራሉ። አንዳንዶች ከቤተሰብ፤ ከዘመድ አዝማድ ጋር በመሰባሰብ፤ ሌሎች ደግሞ ከወዳጆቻቸው ጋር በመገናኘት ያከብሩታል። አንዳንዶች ደግሞ የታመሙ ሰዎችን፤ አቅመ ደካሞችን፣ እስረኞችን በመጠየቅ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም በዓሉን ሲያከብሩ ይታያል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ/ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ