1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢጣልያና የቱኒዝያ ስደተኞች ጎርፍ

እሑድ፣ የካቲት 6 2003

የቱኒዝያ ስደተኞች በባህር በኩል ወደ ኢጣልያ ጠረፍ መጉረፋቸዉ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። በዚህም ጣልያን የአስቸኳይ ጊዜ ደምብ አስፍሮአል። በኢጣልያ ጠረፍ ጥበቃ ሃይል መግለጫ መሰረት ባለፈዉ ሌሊት ብቻ አንድ ሺህ ገደማ የሚጠጉ ስደተኞች ላፓዱዛ ደሴት ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/R0Tg
ምስል AP

ቀደም ባሉት ቀናት ቢያንስ ሶስት ሹህ ገደማ የሚጠጉ የቱኒዝያ ተወላጆች ከስፍኣራዉ መግባታቸዉ አይዘነጋም። የጣልያን ባለስልጣናት የስደተኛዉ መጉረፍ በሚቀጥሉት ቀናትም እንደሚቀጥል ይጠብቃሉ። የሮማ መንግስት ካቢኔ በበኩሉ የጉዳዩን አሳሳቢነት በማጤን የአስቸኳይ ጊዜ ደምብ አስፍኖአል። የኢጣልያ ጠረፍ ጠባቂ ሃይል በመርከቦችና በአዉሮፕላኖች አማካይነት ተጨማሪ ጀልባዎችን ለማግኘት በባህሩ ላይ ፍለጋ እያደረገ ነዉ።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን