1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣልያ የስደተኞች ቀውስ

ሰኞ፣ ሐምሌ 10 2009

የሊቢያ ባለሥልጣናት ስደተኞችን ለመግታት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ይሁን እና ከዛሬ 6 ዓመት አንስቶ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት በሌላት በሊቢያ ህገ ወጥ ሰው አሻጋሪዎች በስደተኞች ብዙ ገንዘብ ማርረፋቸው ቀጥሏል።

https://p.dw.com/p/2ggTn
Boot mit Flüchtlingen im Mittelmeer
ምስል picture-alliance/Italienische Marine/dpa

Beri Rome(Flüchtlingskrise in Italien) - MP3-Stereo

በአሁኑ ጊዜ በብዛት ወደ ኢጣልያ በመግባት ላይ የሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ የኢጣልያ ህዝብ እና የፖለቲከኞችን ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። የኢጣልያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በሊቢያ አድርገው በሜዴትራንያን ባህር በኩል ወደ ኢጣልያ የሚመጡ ስደተኞችን መግታት በሚቻልበት መንገድ ላይ ከሊቢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ጋር ሰሞኑን መክረዋል። የሊቢያ ባለሥልጣናት  ስደተኞችን ለመግታት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ይሁን እና ከዛሬ 6 ዓመት አንስቶ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት በሌላት በሊቢያ ህገ ወጥ ሰው አሻጋሪዎች በስደተኞች ብዙ ገንዘብ ማርረፋቸው ቀጥሏል። የሮሙ ዘጋቢያችን ተክለ እግዚ ገብረ እየሱስ በኢጣልያ የስደተኞች ቀውስ ላይ ያተኮረ ዘገባ ልኮልናል።
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ