1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራና ጅቡቲ

ረቡዕ፣ ሰኔ 2 2002

በኳታር አደራዳሪነት ስምምነት ላይ ደረሱ።

https://p.dw.com/p/NmFp
ኤርትራ በአፍሪካ ህብረት ደስተኛ አይደለችምምስል AP

የኳታሩ ንጉስ ሼክ ሃሚድ ቢን ካሊፋ አል ታኒ ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለመሸምገል ያደረጉት የመጀመሪያው ጥረታቸው ተሳክትዋል። በእርግጥ ለሁለት ዓመታት ኤርትራንና ጅቡቲን ጦር ያማዘዘው የድንበር ውዝግብ ለአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ቀውስን ነበር የፈጠረው። በኳታር ሸምጋይነት የተካሄደው ድርድር ጥሩ ውጤት ተገኝቶበታል። የድርድሩን ውጤት የአፍሪካ ህብረት ተስፋ ሰጪ ሲል አወድሶታል። በስምምነቱ መሰረት ኤርትራ ጦርዋን ከዋንኛዋ የውዝግብ ቀጠና ከሆነችው ራስ ዱሜራ አስወጥታለች።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ