1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ ለተመድ ፀጥታ ምክር ቤት ያቀረበችዉ ጥያቄ

ሰኞ፣ ሐምሌ 27 2007

ኤርትራ በርካታ ዜጎችዋ ሃገርዋን እየለቀቁ ለአስከፊ ስደት የሚዳርጉበትን ሁኔታ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት እንዲያጣራ ጥሪ አቀረበች። የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢውን ፍርድ እንዲያሰጥ የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መግለጫ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/1G90s
Straßenszene in Asmara, Eritrea
ምስል AFP/Getty Images/P. Martell

[No title]


ለኤርትራውያኑ በብዛት መሰደድ የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ባለፈዉ ወር ዘገባዉ የሃገሪቱ መንግሥት ይፈፅመዋል ያለውን የመብት ጥሰት ተጠያቂ ያደረገበትን ምክንያት የኤርትራ መንግሥት ሀሰት ሲል አጣጥሎታል። እንደ መንግሥት ገለጻ፣ ዜጎቹ ሃገሪቱን ጥለው ለሚወጡበት ድርጊት ተጠያቂዎቹ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች እንጂ ተፈፀመ የሚባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አይደለም።

Eritrea Asmara Poster Präsident Afewerki
ምስል Getty Images/AFP/J, Vaughan


ባለፈዉ ሳምንት የኤርትራ መንግሥት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መግለጫ፤ በርካታ ዜጎች ከኤርትራ ወደ አዉሮጳ የመሰደዳቸዉ ምክንያት ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች መሆናቸዉና ስለወንጀሉ የማያሻማ መረጃን እንደሚሰጥ ገልጾአል። በስዊድን ወላጆች የሌላቸዉ ስደተኛ ሕፃናትን በሚረዳዉ ድርጅት ዉስጥ የሚያገለግሉት አቶ ዓለም ዘሞ፤ ሕገ- ወጥ አዘዋዋሪዎች ተገቢዉን ቅጣት እንዲያገኙ የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጠየቀዉን መግለጫ ይደግፋሉ።


የመንግሥታቱ ድርጅት ባለፈዉ ወር ባወጣዉ ዘገባ የኤርትራ መንግሥት ዜጎችን በግዳጅ እንደሚያሰር ቁም ስቅል እንደሚያሳይና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደሚፈፅም መግለፁ ይታወቃል። የተመድን ዘገባ የማይቀበሉት አቶ ዓለም ዘሞ እንደሚሉት የኤርትራ መንግሥት ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ ነዉ የሚሰራዉ። የተባበሩት መንግሥታት ኢርትራዉያን እንዲሰደዱ የዳረጋቸዉን መሠረታዊ ምክንያት መመርመር እንደሚኖርበት ነዉ፤ አቶ ዓለም ዘሞ የተናገሩት።


አዜብ ታደሰ


ነጋሽ መሃመድ