1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ አልሸባብን ትደግፍለች መባሉና የኤርትራ መልስ

ዓርብ፣ ሐምሌ 16 2002

የአሜሪካን ዕንደራሴ ኤድሮይ የሶማሊያን መንግስት የሚወጋውን አልሸባብን ትረዳለች በሚሏት በኤርትራ ላይ ሀገራቸው አስቸኳይ ዕርምጃ እንድትወስድ በጠየቁ ማግስት ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተባለው ቡድን በሰጠው አስተያየት ኤርትራ ለአልሸባብ ድጋፍ ስለ መስጠቷ መረጃ አለመኖሩን ገልጿል ።

https://p.dw.com/p/OTNO
ምስል picture-alliance/ dpa

ሆኖም በአገራት መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን መንስኤ የሚያጠናውና መፍትሄያቸውንም የሚጠቁመው ይኽው ቡድን ኤርትራ ሂዝቡል ኢስላም ለተባለውን ድርጅት ድጋፍ እንደምታደርግ የሚገልፁ ማስረጃዎች መኖራቸውን ጠቁሟል ። ኤርትራ በበኩሏ ሶማሊያ ውስጥ የምደግፈው ቡድን የለም ትላለች ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ

ሽዋዮ ለገሰ