1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ ውድቅ ያደረገችው የአውሮጳ ኅብረት ማዕቀብ

ረቡዕ፣ መጋቢት 15 2013

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራስልስ ባደረጉት ስብሰባ በተለያዩ  አገሮች የሰባዊ መብት ጥሰትን ይፈጽማሉ፣ ያስፈጽማሉ ባሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የማዕቀብ ውሳኔ አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/3r0oM
EU Außenminister Treffen in Brüssel Josep Borrell
ምስል Aris OIkonomou/AFP/Getty Images

ማዕቀቡ የጉዞና የንብረት ማንቀሳቀስ እገዳን ያካትታል

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራስልስ ቤልጂየም ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ በተለያዩ  አገሮች የሰባዊ መብት ጥሰትን ይፈጽማሉ፣ ያስፈጽማሉ ባሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የማዕቀብ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ማዕቀቡ የጉዞ ዕገዳ የሚያደርግና  የንብረት ማንቀሳቀስን የሚከለክል ሲሆን፣ ውሳኔ የተላለፈባቸውም ከቻይና፣ ስሜን ኮሪያ፣ ሊቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራና ሩሲያ የተመረጡ አስራ አንድ ግልሰቦችና አራት ተቋማት መሆናቸው ተገልጿል።  

የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል በሰጡት መግለጫ፣ እርምጃው በሰባዊ መብት ጥሰቶች ላይ ትኩረት ያደረገ  መሆኑን ገልጸዋል፣ የርምጃው ኢላማ ያደረገው የትም ይሁን  የት ግን ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች ላይ ነው። ሁሉም የአውሮፓ  ህብረት የማዕቀብ እርምጃዎች የዓለማቀፍ ህግን ተከትለው ተግባራዊ ይሆናሉ` በማለትም አፈጻጸማቸው አብራርተዋል። 

 የማዕቀቡ ርምጃ ከተወሰደባቸው አራቱ ግለሰቦች፣  በቻይና ዚንጂያንግ ግዛት በሙስሊሞች ላይ በሚፈጸሙ ከፍተኛ  የሰብዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገልጿል። አሜሪካ ብርታኒያና ካናዳ በቻይና ላይ ተመሳሳይ  የማእቀብ እርማጃዎችን በመውሰድ፣ የአውሮፓ ህብረትን እንደተቀላቀሉ የታወቀ ሲሆን፣ እ እ እ በ1989  ዓም በቲአናንመን  አደባባይ ግድያ ምክኒያት ህብረቱ አሳልፎት ከነበረው ማዕቀብ ወዲህ፣  የአውሮፓ ህብረት በቻያና የማዕቀብ ውስኔ ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

EU Außenminister Treffen in Brüssel
ምስል Aris OIkonomou/REUTERS

 ቻይና ህብረቱ ያሳለፈውን የማዕቀብ ውሳኔ ተከትሎ፣ በ10 አውሮፓውያን ግለስቦችና ተቋማት ላይ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች መሆኑን አስታውቃለች። ሚስተር ቦርየል ይህ የቻይና እርምጃ፣ ህብረቱ እየወሰዳቸው ያሉትን ህጋዊ እርምጃዎች አያስቆመውም በማለት.፣ ቻይና እንደዚህ አይነት የአጸፋ እርምጃዎች ውስጥ ከምትገባ፣ ወደ ውይይት እንድትመጣ ጥሪ አቅርበዋል።    
የማዕቀቡ እርምጃ ኢላማ ካደረጋቸው ሶስት የአፍርካ አገሮች አንዷ  በሆነችው ኤርትራ ላይ ማቀቡ የተጣለው፣ የሰባዊ መብት  ጥሰቶች፣ ግድያዎችና የሰዎች መሰወር ወንጀሎች  ምክኒያት መሆኑ ተገልጿል። ማዕቀቡ ኢላማ ያደረገውም በተለይ የኢርትራ  ብሄራዊ ደህንነት ቢሮና ሀላፊው ጀነራል አብርሀ ካሳ ላይ ነው። በውሳኔው ላይ የኢርትራን መንግስት አስተያየት ለማካተት ያደርግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ግን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን፣ `በኢርትራ መንግስትና ህዝብ ላይ ያነጣጠረና መሰረት በሌለው ክስ ላይ የተመሰረተ` ሲል  አጣጥሎታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ  በኢትዮጵያ ላይም የተወያዩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ህላፊው በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ችግር ወዲህ በየእለቱ በርካታ የሰባዊ መብት ጥሰት ዘገባዎች የሚደርሷቸው መሆኑን የገለጹት ሚስተር ቦሪየል፣ ይህ ሁኒታ መቀጠል የሌለበት በመሆኑ አሁንም ግፊታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።` `የስባዊ እርዳታ ያለገደብ በሁሉም ቦታ እንዶደርስ፣  የተፈጸሙ ሰባዊ መብት ጥሰቶች  በገለልተኛ ቡድን እንዲጣሩና የኤርትራ  ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ግፊታችንን እንቀጥላለን በማለት በሰባዊ መብት ጥሰት ተጠያቄ በሆኑ ላይ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች እያጤኑ መሆኑንም አስታውቀዋል። ሀላፊው አክለውም የፊንላድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር  ሚስተር ፔካ ሃቪስቶ ለተመሳሳይ ተለእኮ በድጋሜ ወደ ኢትዮጵያ የሚሂዱ መሆኑንም ገልጸዋል።

EU Außenminister Treffen in Brüssel
ምስል Aris OIkonomou/REUTERS

በሌላ በኩል ሚስተር ሃቪስቶ ፖሎቲኮስ በተሰኘ ጋዜጣ በሰጡት ስተያየት፣ በኢትያጵያ ሰሜናዊ ክፍል ባለው ሁኒታ  ሶስት መሰርታዊ ችግሮች ያዩ መሆኑን አውስተው፤ እነሱም የሰብዊ እርዳታ ጉዳይ፣ የሰባዊ መብት ጥሰቶችና የጦርነቱ መቆምና የሰላም መከበር ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል ። በሁለቱ ማለት የሰባዊ እርዳታ መድረስና የሰባዊ መብት ጥሰቶች ምርመራ ላይ፣  አንዳንድ መሻሻሎች እየታዩ ቤሆንም፣ በሶስተኛውና በማዕከላዊው መንግስትና የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ውይይት እንዲያካሂዱ የማድረጉ  ጉዳይ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ አስታውቀዋል:፣ መንግስት አማጽያኑ መሳሪያቸውን አውርደው እጃቸውነ እንዲሰጡ እየጠየቀ ቢሆንም፣ ይህ ግን በቀላሉ እውን ይሆናል ብለው እንደማይምኑና ለተሻለ ውጤትም የአውሮፓ ህብረት ከአሜርካ ጋር በህብረት ቢሰራ ጥሩ እንደሚሆን ለጋዜጣው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።  

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ