1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ ዳግም የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሆነች

ዓርብ፣ ጥር 13 2003

በሕብረቱ የኤርትራ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አቶ ግርማይ አስመሮም የሹመት ደብዳቤያቸዉን ለሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ለዦን ፒንግ አቅርበዉ ሥራ ጀምረዋል

https://p.dw.com/p/QuLq
ምስል picture-alliance/landov

ኤርትራ ለረጅም ጊዜ እራስዋን ወዳገለለችበት የአፍሪቃ ሕብረት አባልነት በመመለሷ መደሰቱን ሕብረቱ አስታወቀ።ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በገባችዉ የድንበር ዉዝግብና ግጭት ምክንያት መንበሩ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የአፍሪቃ ሕብረት ለኢትዮጵያ ይወግናል በሚል ራሷን ከአባልነት አግልላ ነበር።ሰሞኑን ግን የሕብረቱን የአባልነት መቀመጫዋን ዳግሞ ተረክባለች።በሕብረቱ የኤርትራ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አቶ ግርማይ አስመሮም የሹመት ደብዳቤያቸዉን ለሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ለዦን ፒንግ አቅርበዉ ሥራ ጀምረዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ የአፍሪቃ ሕብረትን የሰላምና የፀጥታ ኮሚሽን ራምታ ላማምራን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ