1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤችአር 128 በአሜሪካ ምክር ቤት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2010

የዩኤስ አሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት እንደራሴዎች ኤችአር 128 በተባለው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንደራሴ ክርስቶፍ ሄንሪ ያዘጋጁት ረቂቅ ሀሳብ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕጎች እንዲሻሩ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/2vnPe
Washington Kongressgebäude bei Nacht
ምስል picture alliance/AP/S. Applewhite

ባለፈው ዓመት ድምፅ ይሰጥበታል ተብሎ በነበረው በኤች አር128  ውስጥ ኢትዮጵያ እንድታሟላቸው ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል የእስረኞች መፈታት አንዱ  ሲሆን ባለፉት ጥቂት ጊዚያት የኢትዮጵያ መንግሥት አንዳንድ እስረኞችን የፈታበት ዓይነቱ ርምጃ በዛሬው ድምፅ አሰጣጥ ላይ ተፅዕኖ ማሳረፍ መቻል አለመቻሉን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይታወቃል። የዋሽንግተኑ ወኪላች መክብብ ሸዋ  እንዳለው፣ ለረቂቁ የውሳኔ ሀሳብ የእንደራሴዎቹን ድጋፍ ለማፈላለግ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚተቹ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን በሚገኘው የዩኤስ አሜሪካ ምክር ቤት ደጃፍ ሰልፍ  ያደርጋሉ። ስለ ኤችአር 128 ድምፅ አሰጣጥ የዋሽንግተኑን ወኪላችንን መክብብ ሸዋን አነጋግረነዋል።

መክብብ ሸዋ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ