1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤድስን እንከላከል

ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2001

የዓለም የኤድስ ቀን ትናንት ታስቦ ሲዉል ህጻናት እንደተወለዱ የሚደረገዉ የኤች አይቪ ቫይረስ ምርመራ ወደፊት ሊገጥም ከሚችለዉ ዉስብስብ የጤና ችግር ሊታደግ ይችላል የሚል መልዕክቱን የተመድ አስተላልፏል።

https://p.dw.com/p/G7lK
ምርመራ!
ምርመራ!ምስል AP

ቫይረሱ በደማቸዉ የሚገኝ ጨቅላ ህፃናት ምርመራና ክትትል ካገኙ በተወለዱ በ12ሳምንት ዉስጥ የጤና ሁኔታቸዉ እንደሚሻሻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ ሳይሆን በመቅረቱ ግን ከተወለዱት ግማሽ ያህሉ የሁለተኛ ዓመት የልደት በዓላቸዉን ሳያከብሩ እንደሚሞቱ ተገልጿል።