1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እልባት ያልተደረገለት የዳርፉሩ ውዝግብ፣

ሐሙስ፣ መጋቢት 11 2006

አፍሪቃ ውስጥ ከውዝግብ ካልተላቀቁት አካባቢዎች አንዲዱ የሱዳን ምዕራባዊ ክፍለ ሀገር ፣ ዳርፉር መሆኑ አይታበልም። የዳርፉር ኑዋሪዎች፤ እ ጎ አ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ ፤ ከሽብር ሁከት ግድያና ስደትገና አልተገላገሉም፤ በመኻሉ በቆዩ ችግሮች ላይ አዳዲስ ታክለዋል።

https://p.dw.com/p/1BTWd
ምስል Getty Images

አንዱም ጋጠ ወጥነት ነው። ከትንንት በስቲያ በሰሜን ዳርፉር ርእሰ ከተማ ኤል ፋሸር፤ ከጋጠ ወጦች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ፖሊስ መገደሉን ፣ የክፍለ ሀገሩ አስተዳዳሪ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
አድልዎን ፣ መረሳትን መንንስዔ በማድረግ በተንቀሳቀሱ የክፍለ ሀገሩ ተወላጆች ላይ እ ጎ አ በ
2003 የካርቱም መንግሥትና ጃንጃዊድ የተሰኙት ዐረባውያን ሚሊሺያ ጦረኞች በጅምላ በወሰዱት የኃይል እርምጃ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዳርፉራውያን መገደላቸውና በሚሊዮን የሚቆጠሩ መሰደዳቸው የሚታወስ ነው።

ስለዳርፉርና መሰል ውዝግቦች አንድ ባለሙያ በማነጋገር ተከታዩን ዝግጅት አጠናቅሬአለሁ።

UNAMID Darfur Sudan
ምስል Reuters

በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም፤ ምዕራባዊት ሰሐራ፤ ሰሜን ማሊ፤ ሰሜን ናይጀሪያ ፣የታላላቆቹ ሃይቆች ምሥራቃዊ ክፍል ፤ ሶማልያና ፤ የመሳሰሉ ገና ከውዝግብ ያልተላቀቁ አካባቢዎች ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪቃ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ተሠማርተውም ፣ ዳርፉር አሁንም ሰላም እንደራቀው ነው።

እስካሁን ማረጋጋትና ሰላም ማሥፈን ያልተቻለበት ምክንያት ምን ይሆን፤ ዓለም አቀፍ የውዝግቦች አጥኚ ድርጅት የአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ተመልካች አብርውስ አታ አሳሞዋ----

«ውዝግቡ እየተጓተተ እንደቀጠለ ነው። ያልከው ልክ ነው። በዳርፉር ልዩ ሁኔታ የምናየውና ከብዙ የአፍሪቃ አገሮች ጋር የሚመሳሰለው ጉዳይ ዋና መንስዔው በቀላል ይጀምርና ቀስ በቀስ እየተወሳሰበ የሚሄድ ነው። ጊዜው ሲራዘም፤ በመኻሉ፣ የተለያዩ አንጃዎች ይፈጠሩና በውዝግቡ የተለያዩ ሂደቶች ጥቅም አለን የሚሉ ይገቡበታል። የዳርፉሩን ውዝግብ መለስ ብለን ስናጤነው፤ በልማትና በመሳሰለው በማዕከላዊው መንግሥት ችላ መባል ፤ መረሳት ነበር። ለአሁኑ ውዝግብ መነሻው የመጀመሪያው ምክንያት አይደለም።ጋጠ ወጥነት ፣ የጎሳ የእርስ- በርስ ግጭትና ሌሎችም ውስብስብ ምክንያቶች የታከሉበት ነው።»

Bildergalerie Kriege im Jahr 2013
ምስል picture-alliance/dpa

አፍሪቃ ውስጥ በየትኛውም ማዕዘን ይሁን፤ ውዝግብ ሲከሠት ባስቸኳይ መላ ካልተፈለገለት ደረጃ በደረጃ እየተቀጣጠለ ፣ እየተስፋፋ ነው መሄዱ እንደማይቀር ምልክቶች ጠቋሚዎች ናቸው። በውዝግቡ የሚሳተፉት ፍላጎታቸው የተለያየ በመሆኑና ስለሚወሳሰብ፤ መፍትኄ ፍለጋ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ቢገባም እንኳ አስቸጋሪነቱ አጠያያቂ አይሆንም። የአፍሪቃ ሕብረትና የአካባቢ ድርጅቶች፣ የምዕራብ ፣ የምሥራቅ ፣ የደቡብና የመሳሰሉት በቀላሉ እልባት ሊደረግለት የሚችል ውዝግብን ለመፍታት የሚቸገሩት ለምን ይሆን!?«የአፍሪቃን ችግሮች በአፍሪቃውያን መፍታት የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ ከአሰቃቂው የሩዋንዳ ጭፍጨፋ በኋላ የመጣ ነው የሚመስለው። ይሁንና በብዙ መልኩ ሲታይ፤ የአፍሪቃን ችግር በአፍሪቃውይን መፍታት ይባል እንጂ፤ ለምሳሌ ያህል የፀጥታ ችግር ሲፈጠር ከዓለም ዙሪያ ይመለከተናል ባዮች ፣ የራሳችን ድርሽ እንወጣለን ሲሉ ዘው ብለው ይገቡበታል። ለዓለም አቀፍ ሰላምና ፀጥታ እርግጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድርሽ የመወጣት ሥልጣን አለው።

የአፍሪቃ ሕብረት፣ አካባቢያዊ ማሕበረሰቦች አሉት። ብዙዎቹ አዳዲሶች ናቸው፤ ውስብስብ ላሉ ችግሮች ባፋጣኝ መላ ለማግኘት ገና ብዚዙ ይቀራቸዋል።»

Bildergalerie 50-jähriges Jubiläum der Afrikanischen Union AU
ምስል M. Longari/AFP/Getty Images

ዳርፉር መታመስ ከጀመረች 11 ዓመት ገደማ ሊሆን ነው። መፍትኄ ለማግኘት የሚደረገው ጥረት እጅጉን አዝጋሚ እንደመሆኑ መጠን ፣ ወጣቱ ትውልድም በአክራሪነት የሚጠመድበት ፈተና ይደቀንበታል። ሱዳን ለዚህ የተንሠራፋ ውዝግብ የተጋለጠችው ለምን ይሆን አብነቱስ ምን ይሆን?

«ሱዳንና ታሪኳን ጠጋ ብሎ ለሚመረምር፣ በማዕከላዊው መንግሥት የተፈጠሩ የማግለል እርምጃዎች ከባድ ችግሮችን ነው ያስከተሉት። የእኩልነት ትግልን የቀሰቀሰው ይኸው ነበር። ካርቱምን ለምሳሌ ያህል ብንወስድ በንፅፅር ማለት ነው የላቀ ልማት የሚታይበት ነው። እናም በሌላው የአገሪቱ ክፍል ይህ ዕድል ሊነፈግ አይገባም የሚል ስሜት ነው የሚያሳድረው፤ የቀድሞው የእኩልነትና ነጻነት ታጋይ ጆን ጋራንግ፣ ያነገቡት የአዲሲቱ ሱዳን ራእይ ያሉት በሱዳን ክፍላተ ሀገር ተቀባይነትን ያገኘ ነበረ።

1980ኛዎቹና በ 1990ኛዎቹ ይኸው ትግል የሚደፋፈር ነበረ። አገሪቱን ከ 2 መክፈሉ፤ ደቡቡ እንዲገነጠል ማድረጉ የክፍላተ ሀገርን የመገለል ጥያቄ አልመለሰም።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ