1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እሥረኞቹ ስዊድናውያን ጋዜጠኞችና የይቅርታ ጥያቄ

ሐሙስ፣ ጥር 3 2004

አሸባሪነትን ደግፈዋል፣ ወደሀገሪቱም በሕገወጥ መንገድ ገብተዋል በሚል ከጥቂት ጊዜ በፊት አስራ አንድ አመት እስራት የተበየነባቸዉ ስዊድናዉያን ጋዜጠኞች ካርሰን ዮሀን እና ማርቲን ሺቢየ በይግባኝ ፈንታ ምሕረት እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ ወሰኑ ተባለ።

https://p.dw.com/p/13iOB
ምስል picture-alliance/dpa



ይህንንም   የጋዜጠኞቹ ቃል አቀባይ ወይዘሮ አና ሮክስቫል ትናንት ለዶይቸቬለ አረጋግጠዋል። ይሁንና፡ ወኪላችን ታደሰ እንግዳው እንደዘገበው፡ ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች እስከዛሬ ከሰዓት በኋላ ለፌዴራሉ የፍትህ ሚንስቴር የይቅርታ ቦርድም ሆነ በእሥር ለሚገኙበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያቀረቡት የይቅርታ ጥያቄ የለም።

ታደሰ እንግዳው
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ