1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤልና የአፍሪቃዉያን ስደተኞች

ሐሙስ፣ የካቲት 13 2006

የእስራኤል መንግስት በርካታ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን ወደዩጋንዳ መላክ መጀመሩን ስማቸዉን ያልተጠቀሰ አንድ የሀገሪቱ ባለስልጣን መግለጻቸዉን አሶሲየትድ ፕረስ ዘገበ።

https://p.dw.com/p/1BCZ2
ምስል Reuters

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከ50 ሺህ በላይ የተገመቱ አብዛኞቹ ኤርትራዉያንና ሱዳናዉያን ስደተኞች እስራኤል ገብተዋል። እስራኤል ቀደም ሲል ወደየሀገራቸዉ የመመለስ እቅድ የነበራት ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ወደሶስተኛ ሀገር ለማሻገር ስትነጋገር ቆይታለች። ወደሀገራቸዉ እንዲመለሱ ከተደረጉት ሌላ ዩጋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል መስማማቷ ሲነገር በአንፃሩ የካምፓላ መንግስት እንዲህ ያለ ዉል የለኝም እያለች መሆኑን ዘገባዉ አመልክቷል። እስራኤል ሃይፋ የሚገኘዉ ዘጋቢያችን ግርማዉ አሻግሬ ካለፈዉ ወር አንስቶ የመላኩ ተግባር መቀጠሉን ገልጾልናል ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ ጠይቄዋለሁ፤

ግርማዉ አሻግሬ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ