1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤል እና አዳዲስ የአይሁዳውያን መኖሪያ ቤቶችን የመገንባት ዕቅዷ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 12 2003

እስራኤል ከኢሩሳሌም በስተደቡብ በሚገኘው የቤታር ኢሊት እና በምዕራባዊ ዳርቻ በሚገኘው የናብሉስ ከተማ አቅራቢያ ባለው የካርኔይ ሾምሮን የአይሁዳውያን ሰፈራ ቦታዎች ላይ ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት አቀደች።

https://p.dw.com/p/Rafs
ምስል picture alliance/landov

ይህ የእስራኤል ዕቅድ በፍልስጤማውያን ዘንድ ትልቅ ቁጣ እና ተቃውሞ አስከትሎዋል። እንደሚታወቀው፡ እስራኤል እአአ በ 1967 ዓም በታካሄደው የስድስት ቀናት ጦርነት ጊዜ ከያዘችው የፍልስጤማውያን ግዛት መካከል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ እንኳን በሰባ አምስት የአይሁዳውያን የሰፈራ ቦታዎች ቢያንስ ሁለት ሺህ መኖሪያ ቤቶች መስራትዋን በእስራኤል እና በፍልስጤማውያን መካከል የቀጠለው ውዝግብ እንዲያበቃ የሚታገለው ፒስ ናው የተሰኘው ሰላም አፈላላጊ ቡድን ያወጣው መግለጫ አስታውቋል። ይህ አሁን እስራኤል በምዕራባዊው ዳርቻ የሰፈራውን ቦታ ለማስፋፋት የወጠነችው ዕቅዷ እክል በገጠመው የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ሂደት ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ የሀይፋውን ወኪላችን ግርማ አሻግሬን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት ጠይቄው ነበር።

ግርማ አሻግሬ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ