1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤል ወንጀልና የአፍሪቃዉያን እጣ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 24 2005

ቴልአቪቭ እስራኤል አንድ ኤርትራዊ ወጣት ፈጽሟል ያሉትን አስገድዶ የመድፈር ተግባር በመቃወም ከመቶ በላይ የተገመቱ ዜጎች ለተቃዉሞ ሰልፍ መዉጣታቸዉ ተሰምቷል። የ83ዓመቷን አዛዉንት በመድፈር የተጠረጠረዉ በስደት እስራኤል ዉስጥ የሚገኝ የ20 ዓመት ወጣት ነዉ ተብሏል።

https://p.dw.com/p/17Cbl
ምስል Reuters

 ይህን መሰሉ ድርጊትም ሆነ ወንጀል ጋ በተጋናኘ ኅብረተሰቡ አትኩሮ የሚመለከታቸዉ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ከሃገር እንዲወጡ የሚጠይቁ ወገኖች ተበራክተዋል። በተለይም የኤርትራ ዜጎች ከእርስ በርስ ፀብ አስንቶ በተለያዩ ተግባራት ዓይን ዉስጥ መግባታቸዉና የመገናኛ ብዙሃኑን ትኩረት መሳባቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። እስራኤል ሃይፋ የሚገኘዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬን ስለጉዳዩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።  

ግርማዉ አሻግሬ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ