1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤል የአሜሪካን ም/ቤት አባላትን ወደሃገርዋ እንዳይገቡ ከለከለች

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2011

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ «ሃገራችሁ ተመለሱ »ሲሉ የዘለፏቸውን የሁለት የአሜሪካን ምክር ቤት አባላትን የእስራኤል ጉብኝት እንደማትፈቅድ እስራኤል አስታወቀች። የእስራኤል ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትዚፒ ሆቶቭሊ ዛሬ ለእስራኤል ራድዮ«ውሳኔ ላይ ተደርሷል፤ውሳኔውም እነርሱ እሥራኤል እንዳይገቡ መከልከል ነው።»

https://p.dw.com/p/3Nysk
Ilhan Omar und Rashida Tlaib
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. S. Applewhite

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ «ሃገራችሁ ተመለሱ »ሲሉ የዘለፏቸውን የሁለት የአሜሪካን ምክር ቤት አባላትን የእስራኤል ጉብኝት እንደማትፈቅድ እስራኤል አስታወቀች። የእስራኤል ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትዚፒ ሆቶቭሊ ዛሬ ለእስራኤል ራድዮ«ውሳኔ ላይ ተደርሷል፤ውሳኔውም እነርሱ እሥራኤል እንዳይገቡ መከልከል ነው።» ብለዋል።ምክትል ሚኒስትሩ የኛን የህልውና መብት የማይቀበሉን ወደ ሃገራችን አናስገባም ሲሉም አክለዋል።ሁለቱ ዴሞክራት የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ እንደራሴዎች ራሺዳ ታሊብ እና ኢሃን ኦማር በእስራኤል ጉዞአቸው የዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻን እና ምሥራቅ እየሩሳሌምን የመጎብኘት እቅድ ነበራቸው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ የታይብ እና የኦማር የእስራኤል ጉብኝት እንዲከለከል እስራኤልን ጠይቀው ነበር።    

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ