1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤል፥ ዩናይትድ ስቴትስና መካከለኛዉ ምሥራቅ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 29 2002

የሁለቱ መሪዎች ዉይይት ባለፈዉ የካቲት እንደተደረገዉ ቀዝቃዛ ሳይሆን በመግባባትና በጥብቅ ወዳጅነት መንፈስ የሚደረግ ነዉ ተብሎ ይጠበቃል

https://p.dw.com/p/OC4P
ምስል AP

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቢንያሚን ኔታንያሁ ዩናይትድ ስቴትስን ለመጎብኘት ዋሽንግተን ገብተዋል።ኔታንያሁ ዛሬ ማምሻቸዉን ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተዉ ይነጋገራሉ።ጉብኝት ንግግሩ ባለፈዉ ወር ሊደረግ ታቅዶ ነበር።ይሁንና የእስራኤል ጦር ለጋዛ ሕዝብ የርዳታ እሕል የጫነች መርከብን ወርሮ እርዳታ አቀባዮችን በመግደሉ ምክንያት እስካሁን ዘግይቶ ነበር።የሁለቱ መሪዎች ዉይይት ባለፈዉ የካቲት እንደተደረገዉ ቀዝቃዛ ሳይሆን በመግባባትና በጥብቅ ወዳጅነት መንፈስ የሚደረግ ነዉ ተብሎ ይጠበቃል።የጉብኝቱን አላማና የዉይይቱ መንፈስ ወደ ነበረበት የተመለሰበትን ምክንያት በማስመልክት የየሩሳሌም ዘጋቢያችንን ዜናነሕ መኮንን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ