1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እንቦጭን ከጣና ለማስወገድ የተሰራው ሥራ ምን አሳካ?

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2012

ጣናን በቅርብ የሚከታተሉት ዶክተር ሽመልስ አይናለም እንደሚሉት በእንቦጭ መስፋፋት ምክንያት በሐይቁ ዙሪያ የነበረው የግጦሽ መሬት ጠፍቷል፤ ወቅት ጠብቀው ከሌሎች ዓለማት ወደ ጣና ይበሩ የነበሩ ከ120 በላይ አዕዋፋት ቁጥራቸው ተመናምኗል። ይባስብሎ ኢትዮጵያ ከሱዳን እና ግብፅ የምትነታረክበትን ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ሊያሰጋ እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ

https://p.dw.com/p/3dDNT
Äthiopien Kampagne Save Lake Tana
ምስል Kalkidan Tsena

እንቦጭ እና ጣና

እንቦጭን ከጣና ላይ ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ እያለ ሁለት አመታት ገደማ አስቆጠረ። የአካባቢው ገበሬዎች እና የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች እንደሚሉት እንቦጭ በሐይቁ የበለጠ እየሰፋ ሥጋት ሆኗል።

ጣናን በቅርብ የሚከታተሉት ዶክተር ሽመልስ አይናለም እንደሚሉት በእንቦጭ መስፋፋት ምክንያት በሐይቁ ዙሪያ የነበረው የግጦሽ መሬት ጠፍቷል፤ ወቅት ጠብቀው ከሌሎች ዓለማት ወደ ጣና ይበሩ የነበሩ ከ120 በላይ አዕዋፋት ቁጥራቸው ተመናምኗል።

የዓለም የአካባቢ ቀን ዛሬ ታስቦ ውሏል። በዚህ ቀን መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች የጣና ሐይቅ  እጣ ፈንታ ነው። የእንቦጭ አረምን ከሐይቁ ለማስወገድ የተሰራው ሥራ ምን አሳካ? ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ዶክተር ሽመልስ አይናለም የታዘቡትን ለዶይቼ ቩለ አስረድተዋል። ዶክተር ሽመልስ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግብርና እና  አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር እና በብሉ ናይል የውኃ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ናቸው።

ቃለ ምልልሱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ

ታምራት ዲንሳ