1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እጩዎችና የእጣ መለያዉ

ሐሙስ፣ የካቲት 19 2007

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ እጩዎና አንዳንድ የግል ተወዳዳሪዎች በመጪዉ ምርጫ እንዳይሳተፉ በእጣ መገለላቸዉ እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1EiFC
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአንድ የምርጫ ክልል ከ12 እጩዎች የሚወዳደሩ ከሆነ ቀሪ ስድስቱ በእጣ የመለየቱ ጉዳይ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 38 የተቀመጠዉን የምመርጥና የመመረጥ መብትን እንደሚጋፋ አንዳንድ በፖለቲካ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አመልክተዋል። አንድ የሕግ ምሁር በበኩላቸዉ አሠራሩ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 38ን አይጋፋም በአንፃሩ ድምፅ በ12 ቦታ ተበትኖ በስም አብላጫ ድምፅ አብዛኛዉ ባልመረጠዉ ሰዉ እንዲተዳደር የሚያስገድድ ነዉ፤ ይህም ለገዢዉ ፓርቲ የሚያመች አሠራር ነዉ ሲሉ ተችተዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ