1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦህዴድ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ጥሪ አቀረበ

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ጥር 30 2010

ኦህዴድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የአቋም ልዩነት ቢኖረዉም የዉይይት ባህልን ለማዳበርና ለሕዝቦች አማራጭ ኃሳቦችን ለማቅረብ ሲባል በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። «የኃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ የሚያስችል አሰራርና ባህል ማዳበር እንደምያስፈልግም ገልጿል።

https://p.dw.com/p/2sHeN
Äthiopien, Adama
ምስል DW/M. Yonas Bula

የኦህዴድ ዝግጁነት

ድርጅቱ በአገር ዉስጥና በዉጭ ከሚገኙት የፖለትካ ፓርቲዎች ጋር ለመሥራት ፍቃደኛ እና ዝግጁ መሆኑ ን ገልጿል ። አገር ዉስጥም ሆነ ዉጭ ያሉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኦህዴድ ላይ የተወሰነ ቁጥብነት ቢኖራቸዉም ዉሳኔዉን በበጎ ወስደውታል።

ኦህዴድ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የአቋም ልዩነት ቢኖረዉም የዉይይት ባህልን ለማዳበርና ለሕዝቦች አማራጭ ኃሳቦችን ለማቅረብ ሲባል በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። በገዥዉና በታቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያለዉ ግኑኝነት «እንደ ነብር ዥንጉርጉር» ሲል የገለፀዉ ኦህዴድ «የኃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ የሚያስችል አሰራርና ባህል ማዳበር እንደምያስፈልግም» በመግለጫዉ ጠቅሷል።

የቀድሞ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና አሁን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገብሩ ገብረማርያም ኡቱራ የኦህዴድን አቋም መግለጫ በበጎ ቢመለከቱም በአጋርቱ፤ በተለይም በኦሮሚያ ዉስጥ ብዙ ሊነሱ የሚገባቸዉ ጉዳዮች አሉ ይላሉ። አሁን በአሮሚያ ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት የአሁኑ ደረጃ ላይ ሳይደርስ በፊት ፓርቲያቸዉ ኦህዴድን ለዉይይት ቢጠይቅም መልስ እንዳላገኙ አቶ ገብሩ ይናገራሉ። ከክልልም አልፎ በአገር አቀፍ ደረጃ ፓርትያቸዉ ከኢሕአዴግ ጋር ለመወያያት ዝግጁ መሆኑን ካላለፉት 10 ዓመታት በላይ ሲጠይቁ ብቆዩም መልስ እንዳላገኙ አቶ ገብሩ ገልፃዋል። አሁን ኢሕአዴግ ከተቃዋም ፓርትዎች ጋር እያካሄድኩ ነዉ የሚለዉ ዉይይት ዉስጥ ፓርትያቸዉ አለመሳተፉን እንዲህ ያብራራሉ።

ከአገር ዉጭ ካሉት የፖለትካ ፓርቲዎች ዉስጥ የኦህዴድን ጥሪ የተቀበለዉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ነዉ። ግንባሩ ትላንት ባወጣዉ መግለጫ ጥሪዉ ወቅታዊ እና አቅጣጫዉም ትክክለኛ መሆኑን ጠቅሶ ከኦህዴድ ጋር አብሮ ለመስራትም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ኦዴግ ቀደም ሲል ከኢሕአዴግ ጋር ለመወያየት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን የሚያስታዉሱት የግንባሩ ቃልአቀባይ ዶክተር በየን አሶባ ኢሕአዴግ ፍቃደኛ ስላልነበረ ከአጋር እንዲወጡ መገደዳቸዉን ጠቅሰዋል። ኦዴግ፣ ኢሕአዴግ «አሸባሪ» ሲል ከፈረጀዉ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ጥምረት መፍጠሩና አርበኞች ግንቦት ሰባትም ኢሕአዴግ በኃይል ለማስወገድ «ጠመንጃ» ማንሳቱ ይታወቃል።

ኦህዴድ እንድ አይነት ዉሳኔ ላይ ለመድረስ ረጅም ጉዞ ተጉዞ ነዉ የሚሉት ዶክተር በየን አሁን ጥሪውን በተግባር ማሳየት አለበት ብለዋል።  

መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ