1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦስካር ፒስተርየስና የተሰጠው ብይን

ዓርብ፣ መስከረም 2 2007

ኦስካር ፒስተርየስ ጊዜ ጠብቆ ፤ አቅድ አውጥቶ ሰው የገደለ ወንጀለኛ አይደለም ሲሉ ዋና ዳኛ በየኑ ።የካቲት 7 ቀን 2005 ዓ ም ፣ ፈረንጆቹ (Valentine Day) በሚሉት ፣ ወንዶች ለሚያፈቅሯ ቸው የአበባ ሥጦታ በሚያበረክቱበት ዕለት ፣

https://p.dw.com/p/1DBaF
ምስል picture-alliance/K. Ludbrook

መኖሪያ ቤቱ ውስጥ በመጸዳጃ ክፍል ውስጥ በነበረችው ፍቅረኛው ላይ ፣ ከበር ጥይት በማርከፍከፍ ሕይወቷን ያሳለፈው ፣ በፓራሊምፒኪስ ፣ የአካል ጉዳተኞች ኦሊምፒክስ ውድድር ዝነኛ የሆነው ደቡብ አፍሪቃዊው ኦስካር ፒስተርየስ፣ አቅድ አውጥቶ ፤ ጊዜ ጠብቆ ግድያ አልፈጸመም፣ ይህን የሚያረጋግጥ በቂ ማስረጃ አልቀረበም ሲሉ ዋና ዳኛ ቶኮዚሌ ማሲፓ በይነዋል።

Oscar Pistorius Freispruch
ምስል Reuters/K. Ludbrook

ኦስካር ፒስተርየስ ሌባ ቤቴ የገባ መስሎኝ በደመ ነፍስ ነው የተኮስሁ በማለት ነበር ሲከራከር የቆየው። ይሁንና በፍርሃትም ይሆን በግድየለሽነት በወሰደው ርምጃ ፣ የሰው ሕይወት አጥፍቷል ሲሉ የፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ አስታውቀዋል። በመሆኑም ፣ ጥቅምት 3 ቀን ሌላ ብይን እንደሚሰጥ እንደሚሰጥ ነው የተገለጠው። የተጠቀሰው ዓይነት በደንታቢስነት የሰው ሕይወት የማጥፋት ርምጃ ፣ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ 15 ዓመት ያህል በእሥራት ያስቀጣል። ስለ ብይኑ ከህዝብና ከመገናኛ ብዙኀን የተሰነዘረው አስተያየት ምን የሚል ነው? በዚያው በፕሪቶሪያ፣ ደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያውያን ማሕበረሰብ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ ደረጀ መኮንን ---

ዳኛ ቶኮዚሌ ማሲፓ ፤ በሙያቸው የታወቁና ፤ የህግን ልዕልና እንጂ ፣ የዚህ የዚያ ወገን ፤ ነጭ --ጥቁር የሚል ነገር ዋጋ እንደሌለው ያሳዩ አስተዋይ ዳና ናቸው የሚሉም አልታጡም። ይሁንና ብይናቸው፤ ከከሳሽ ጠበቆች ብቻ ሳይሆን በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ረገድ ባለሙያዎች ከሆኑ የሕግ ጠበብትም ተቃውሞ አልቀረለትም። ፒስተርየስ በግድያ ወንጀለኛ ነው የሚል ብይን ቢሰጥ ኖሮ ቢያንስ የ 25 ዓመት እሥራት ነበረ የሚያጋጥመው። የይግባኝ ክስ ይቀርብ ይሆን?

Protest gegen das Oscar Pistorius-Urteil vor dem Gericht in Pretoria 11.09.2014
ምስል Getty Images/C. Furlong

ኦስካር ፒስተርየስ በደቡብ አፍሪቃ የታወቀ ፤ ዝነኛ የአካል ጉዳተኛ አትሌት ነው። ፍቅረኛውን በተኮሰው ጥይት ለሕልፈተ ሕይወት መዳረጉ ብቻ ሳይሆን ፤ ከዚያ ቀደም ሲልም ሽጉጥ ታጥቆ በመዞር፤ ጆሐንስበርግ ውስጥ በአንድ የምግብ አዳራሽ ብዙ ሰዎች በተገኙበት፣ ከጠረጴዛ ሥር መተኮሱ ፣ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ጥይት መሰብሰቡና ከመኪና ጣሪያ ላይ መተኮሱም የተመዘገበና ክስ ቀርቦ የተሻረለት መሆኑ ተወስቷል።

እርግጥ የከሳሽ ጠበቆችና የተከላካይ ጠበቆች ተጻራሪ አቋም ሊኖራቸው እንደሚችል የሚያጠራጥር አይደለም። በገለልተኛነት የሚከታተለው ክፍል ፤ እዚህ ላይ ማሕበረሰቡ ምን ይላል?

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ