1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦነግ አባላቴ እጅ አልሰጡም ይላል፤

ረቡዕ፣ ጥር 12 2002

ሰሞኑን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት መሆናቸዉ የተገለፀ ከአንድ መቶ የሚልቁ ታጣቂዎች ከነመሣሪያቸዉ ለመንግስት እጅ መስጠታቸዉን አስመልክተን መዘገባችን ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/Lbtt
ምስል AP GraphicsBank/DW

በኤርትራ የሚገኙት የአንደኛዉ ወገን የኦነግ ሊቀመንበርም እጅ ሰጡ የተባሉት ከግንባሩ ከወጡ ዓመት ልፏቸዋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን በዚሁ ላይ ያነጋገራቸዉ የግንባሩ ቃል አቀባይም ይህንኑ አጠናክረዋል። ኦነግ ለሁለት መከፈሉ ይታወቃል። ከግንባሩ ተለዩ ስለሚባሉት እጅ ሰጪዎች ለማጣራት አስመራ የሚገኙትም ሆኑ አሜሪካን ያሉት የሌላኛ ቡድን የአመራር አባላት ላደረግነዉ ሙከራ ትብብር አላደረጉም።

አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ