1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦዉንግ ሳን ሱ ቺ በብረስልስ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 26 2009

የማንያመር መንግሥት ከፍተኛ አማካሪና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ኦዉንግ ሳን ሱ ቺ በአዉሮጳ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን በትናንትናዉ እለት ከአዉሮጳ ኅብረትና ከቤልጂየም ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። ሱ ቺ ሃገራቸዉን ወክለዉ ወደ አዉሮጳ ሲመጡ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2cONJ
Belgien | Pressekonferenz Federica Mogherini und Aung San Suu Kyi
ምስል Reuters/E. Vidal

MMT Ber. Brüssels (Aung San Suu Kyi in Brüssels) - MP3-Stereo


ለበርካታ ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት ሱቺ፤ አምባገንን ስርዓትን በመታገል ላሳዩት ጽናት በጎርጎረሳዊዉ 1991 ዓ,ም የሠላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ በመሆንም ድምፅ ለሌላቸዉ ድምፅ የሆኑ በመባል ተወድሰዋል። ወይዘሮዋ ከዚህ ቀደም በተቃዋሚ መሪነትና በኖቤል ሽልማት አሸናፊነታቸዉ በአዉሮጳ ኅብረት ጉብኝት ያደረጉ ቢሆንም የማንያመር መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን ሆነዉ ጉብኝት ሲያደርጉ ግን ይህ የመጀመርያቸዉ ነዉ።  የብረስልሱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል።


ገበያዉ ንጉሴ 
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ