1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ የኦነግ አመራሮች አቀባበል ሰላማዊ እንዲሆን ጠየቁ

ዓርብ፣ መስከረም 4 2011

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ እና ሰማያዊ ፓርቲ ነገ ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚደረገው አቀባበል ሰላማዊ እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ። የኦሮሞ ፌድራሊት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ሕዝቡ ሊደማመጥ ይገባል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/34tGT
Äthiopien Proteste | Mulatu Gamachu
ምስል DW/M. Yonas Bula

(Beri. AA) OFC & Blue Party press conference - MP3-Stereo

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ እና ሰማያዊ ፓርቲ ነገ ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ሰላማዊ እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ። የኦሮሞ ፌድራሊት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ሕዝቡ ሊደማመጥ ይገባል ብለዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ እንግዶቹን ለመቀበል የብሔር እና የቋንቋ ልዩነት ገደብ ሊሆን አይገባም ብለዋል። የአዲስ አበባዉ ዘጋብያችን ተጨማሪ ዘገባ አለው።


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር


እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ