1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከልማት እርዳታዉ ይልቅ የሰብአዊ መብት ይቅደም

ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 2003

የጀርመኑ ለአደጋ የተጋለጠ ህዝብ መብት ተቆርቋሪዉ ድርጅት በኢትዮጽያ የሰብአዊ መብት ይዞታ እስካልተስተካከለ ጀርመን የምትሰጠዉን የልማት እርዳታ መቀጠል የለባትም ሲል መግለጫዉን አዉጥቶአል።

https://p.dw.com/p/RWEL

ድርጅቱ ይህን ያስታወቀዉ ጀርመን ለኢትዮጽያ የምትሰጠዉን የልማት እርዳታ በአዲስ መረሃ-ግብር ለመፈጸም ዛሪ ሁለቱ መንግስታት ለድርድር ለመቅረብ ሲዘጋጁ ነዉ። በዚሁ ጉዳይ ዙርያ ለአደጋ የተጋለጠ ህዝብ መብት ተቆርቋር ድርጅት ያወጣዉን መግለጫ በማስመልከት የድርጅቱ ተጠሪ ኡልሪሽ ዴሉስን አዜብ ታደሰ አነጋግራለች።

በኢትዮጽያ ያለዉ የሰብአዊ መብት ሁኔታ እስካልተስተካከለ ጀርመን ለኢትዮጽያ የምትሰጠዉን የልማት እርዳታ መቀጠል የለባትም ሲል የጀርመኑ ለአደጋ የተጋለጠ ህዝብ መብት የሚቆረቆረዉ ድርጅት Gesellschaft für Bedrohte Völker ባወጣዉ መግለጫዉ አስጠንቅቆአል። ድርጅቱ ይህን መግለጫ ይፋ ያደረገዉ ጀርመን ለኢትዮጽያ የምትሰጠዉን የልማት እርዳታ በአዲስ መረሃ-ግብር ለመቀጠል ከኢትዮጽያ መንግት ጋር ዛሪ ለመደራደር ዝግጅት ላይ ሳለች ነዉ። ለጥቃት የተጋለጠ ህዝብ መብት የሚቆረቆረዉ ድርጅት ተጠሪ ኡልሪሽ ዲሉስ ድርጅታቸዉ ስላወጣዉ መግለጫ

« የጀርመን ፊደራል መንግስት በቅርቡ ባወጣዉ በአዲሱ የአፍሪቃ ፖሊሲዉ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ተቀዳሚዉን ቦታ መያዝ አለበት። ማንኛዉም ከአፍሪቃ ጋር የሚሰሩ የጀርመን ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች እዚህ ላይ የጀርመን የልማት ተራድኦንም ያጠቃልላል፣ አፍሪቃ ዉስጥ በሚያደርጉት የልማት እንቅስቃሴ የሰብአዊ መብት ጉዳይን የመጀመርያ መርሆአቸዉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በዚህም ዛሪ የጀርመን እና የኢትዮጽያ መንግስት የሚያደርጉት የልማት እርዳታ ድርድር የመጀመርያዉ ምዕራፍ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ማስከበር መሆን አለበት እንላለን።

Gesellschaft für bedrohte Völker Logo Grafik

አንደ ኡልሪሽ ዴሉስ ጀርመን ለኢትዮጽያ የምታቀርበዉን የልማት እርዳታ አስመርኩዛ በኢትዮጽያ የሰብአዊ መብት ጉዳይ እንዲሻሻል የጀርመን መንግስት ጫና እና ግፊት እንዲያደርግ ነዉ። ድርጅቱ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ በኢትዮጽያ መንግስት አስተያየት ለዉጭ ባለሃብቶች ሰፋፊ የእርሻ መሪትን ለመስጠት የህዝብን የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል በሚል 700 .000 ያህል ህዝብ ከመኖርያ ቀየዉ ተፈናቅሎ ሌላ ቦታ እንዲኖር ሆንዋል። ይህ በተለይ በገጠሩ ያለዉን ህዝብ ስብዕና ተጋፍቶአል ነዉ። ለአደጋ የተጋለጠ ህዝብ መብት ተቆርቋሪዉ ድርጅት ተጠሪ በበኩላቸዉ በኢትዪጽያ ይላሉ

«የሰዉ ልጅ መብትን የሚጥሱ አንዳንድ ጉዳዮች ታይተዋል። ለምሳሌ አሁን በቅርቡ በኢትዮጽያ ዉስጥ የተደረገዉ አዲሱ የህዝብ የሰፈራ ጉዳይ፣ በአርሻ ልማት ንዋያቸዉን ማስፍሰስ ለሚፈልጉ የዉጭ ባለሃብቶች ሰፋፊ የመሪት ይዞታን የመስጠቱ ሁኔታ የሰብአዊ መብት የመጣስን የሚጠቁሙ ናቸዉ። በኢትዮጽያ የሰብአዊ መብት ይዞታን አስመልክቶ ከጀርመን ፊደራል መንግስት በጽሁፍም ሆነ በቃል እንደምንሰማዉ በኢትዮጽያ ለባለሃብት የመሪት ይዞታን ለማዳረስ እና የህዝብ ሰፈራ ጉዳይ በገጠሩ ነዋሪ ሙሉ ፍላጎት እንደተከናወነ ነዉ፣ የኢትዮጽያ መንግስት በማስረገጥ የሚገልጸዉ። እዚህ ላይ ግን የኢትዮጽያ መንግስት የሰዉ መብት ጥሻለሁ ብሎ ማስረጃ ይልካል ብሎ መጠበቅ የማይታመን ነዉ። ስለዚህ ይህን ነገር ለማጤን የጀርመን ፊደራል መንግስት አንድ ገለልተኛ የሆነ ባለሞያዉ በቦታዉ በመላክ ነገሩን ማጣራት ይኖርበታል። በእኛ አመለካከት በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከጀርመን አኳያ ጥቂት ግፊት ነዉ የተደረገዉ።

Ulrich Delius Gesellschaft für bedrohte Völker
ዴሉስምስል Gesellschaft für bedrohte Völker

የጀርመኑ የልማት ተራድኦ ድርጅት በኢትዮጽያ ከልማት እንቅስቃሴዉ ሌላ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ አጢኖ አልመረመረም የሚሉት ጀርመኑ ለአደጋ የተጋለጠ ህዝብ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ተጠሪ ኡሊሽ ዲሉስ የጀርመን መንግስት ይላሉ

እስካሁን ጀርመን መንግስት በኢትዮጽያ ስላለዉ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ትክክለኛ ምርመራ እና ጥናት ያደረገ አይመስለንም ምንም እንኳ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በኢትዮጽያ ያለዉን የሰብአዊ መብት ገፈፋ በተመለከተ ብዙ ሪፖርቶችን በይፋ ቢያደርጉም። የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚኒስቴር በልማት እንቅስቃሴ ለምሳሌ የሰፈራዉ ጉዳይ በተመለከተ የህዝቡ ፍላጎት መጠየቁ አልተረጋገጠም። ምንም እንኳ ኢትዮጽያ ለፖለቲካ ስትራቴጂ ጀርመን የምትፈልጋት አገር ብትሆንም የሰብአዊ መብት ጉዳዪች መጣሳቸዉን በተመለከተ ብዙ ሪፖርቶች ቢጻፉም አይንን ጨፍኖ ማለፍ ጥሩ አይመስለንም።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ