1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከምርጫ ማግስት በቀረበው የሽግግር መንግስት ጥሪ እና ተቃዉሞ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 26 2013

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር “በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም እየተሰራጨ ነው” ያለውን “የሽግግር መንግስት” አዋጅ እንደማይቀበል ገለፀ፡፡

https://p.dw.com/p/3vyqm
Äthiopien Statement Oromo Liberation Front
ምስል DW/Seyoum Getu

ኦነግ እና ኦፌኮ ያቀረቡትን የሽግግር መንግስት ምስረታ ጥያቄ ከኦነግ የተነጠለው ቡድን ተቃውሞታል

ከምርጫ ማግስት በቀረበው የሽግግር መንግስት ጥሪ የኦነግ አመራሮች ውዝግብ

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር “በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም እየተሰራጨ ነው” ያለውን “የሽግግር መንግስት” አዋጅ እንደማይቀበል ገለፀ፡፡

ፓርቲው ባወጣው ባለሰፊ አተታ መግለጫው በአቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይፋዊ ገፅ የወጣውን የሽግግር መንግስት ምክረ ሀሳብ ጥሪንም ነቅፎ አቋሙን ገልጾበታል፡፡

የፓርቲው ባለስልጣናት ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያም ፓርቲያቸው ስልጣን በምርጫ እንዲተላለፍ ያምናል ብለዋል፡፡

ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኮልናል፡፡