1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሳሽ ያጡት እነ ኤልያስ ለጠቅላይ ሚኒሥትሩ አቤቱታ አቀረቡ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2009

ከአምስት ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ፖለቲከኛው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒሥትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአቤቱ ደብዳቤ ፃፉ።

https://p.dw.com/p/2cclC
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

The detained journalist and politician wrote an appeal for PMHD - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግሥት ከደነገገው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የታሰሩት ኤልያስ እና ዳንኤል እስካሁን በይፋ ክስ አልተመረተባቸውም። በእስር ላይ «ተጉላልተናል» ያሉት ጋዜጠኛ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒሥትሩ ለፃፉት የአቤቱታ ደብዳቤ የሚሰጣቸው ምላሽ የታወቀ ነገር የለም። አዲስ አበባ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ያነጋገራቸው የተጠርጣሪዎቹ ባልደረባ አቶ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገቢውን የሕክምና ክትትልም አለማግኘታቸው ተናግረዋል። 
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር 
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ