1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት እርምጃ 

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 2012

በተለያዩ የሳዑዲ አረብያ  እስር ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች በኮሮና ምክንያት በምህረት እየተለቀቁ ነው።ከመካከላቸው 1000የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/3aiqI
Symbolbild: Illegale Arbeiter in Saudi Arabien
ምስል picture-alliance/AP/E. Asmare

ኢትዮጵያዉን እስረኞች ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ሳዑዲ አረቢያ የኮሮና ተህዋሲን ሥርጭት ለመከላከል የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው።በተለያዩ የሳዑዲ አረብያ  እስር ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች በኮሮና ምክንያት በምህረት እየተለቀቁ ነው።ከመካከላቸው 1000የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል። ታራሚዎቹን ከሳውዲ ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዙ በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረብያ መንግሥታት ስምምነት እየተከናወነ መሆኑን የጅዳ ቆንስል መ/ቤት የበላይ አምባሳደር አብዱ ያሲን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በግምት ወደ 6000ያህል የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ወህኒ ቤቶች  አሉ ተብሎ ይገመታል።

ነቢዩ ሲራክ 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ