1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያዉያን

ሐሙስ፣ ሰኔ 22 2009

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት «ሕገ-ወጥ» ያላቸዉ የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ የሰጠዉ ቀነገደብ ቢጠናቀቅም  በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን አሁንም ወደ ሐገራቸዉ አልተመለሱም።

https://p.dw.com/p/2febl
Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

(Beri.AA) Ethiopian MoF-Saudi Arabia Returnees - MP3-Stereo

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ከሐገሩ እንዲወጡ ያስገደዳቸዉ ኢትዮጵያዉያን ብዙ ሳይንገላቱ ወደ ሐገራቸዉ እንዲገቡ ለማድረግ የጀመረዉን ጥረት እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት «ሕገ-ወጥ» ያላቸዉ የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ የሰጠዉ ቀነገደብ ቢጠናቀቅም  በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን አሁንም ወደ ሐገራቸዉ አልተመለሱም።የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀቁ ሳዑዲ አረቢያ የሰጠችዉን ቀነ-ገደብ እንድታራዝም የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ጠይቋል።

ዮኃንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ