1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከስደተኝነት እስከ ምክር ቤት አባልነት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 25 2005

በጀርመን የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተመሳስለው ለመኖር ፣ ሥራ አጥ ላለመሆን ፣ አድልኦንም ለመከላከልና የተሻለ የትምህርት እድል ለማግኘት የውሳኔ ሰጭ አካል መሆን ነው የተሻለው አማራጭ ይላሉ ። ርሳቸው እንደሚሉት ከውጭ ሆኖ ለውጥ የማምጣቱ እድል ዝቅተኛ ነው ።

https://p.dw.com/p/16vl6
Der Bremer Abgeordnete Elombo Bolayela vor der Bremischen Bürgerschaft (Landtag). Er ist ein Migrant aus der Demokratischen Republik Kongo und 2011 für die SPD als erster afrikanischstämmiger Abgeordneter in einen deutschen Landtag eingezogen. Foto DW/Philipp Sandner, 2012 in Bremen
ምስል DW
Der Bremer Abgeordnete Elombo Bolayela in der Bremischen Bürgerschaft (Landtag). Er ist ein Migrant aus der Demokratischen Republik Kongo und 2011 für die SPD als erster afrikanischstämmiger Abgeordneter in einen deutschen Landtag eingezogen. Foto DW/Philipp Sandner, 2012 in Bremen
ምስል DW
Der Bremer Abgeordnete Elombo Bolayela in der Bremischen Bürgerschaft (Landtag). Er ist ein Migrant aus der Demokratischen Republik Kongo und 2011 für die SPD als erster afrikanischstämmiger Abgeordneter in einen deutschen Landtag eingezogen. Foto DW/Philipp Sandner, 2012 in Bremen
ምስል DW
Bremer Baumarkt, zweite Arbeitsstelle von Herrn Bolayela. Er ist ein Migrant aus der Demokratischen Republik Kongo und 2011 für die SPD als erster afrikanischstämmiger Abgeordneter in einen deutschen Landtag eingezogen. Foto DW/Philipp Sandner, 2012 in Bremen
ምስል DW

አሁን ለደረሱበት ሃላፊነት በመብቃት በጀርመን የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ናቸው ። ከ20 አመት በፊት ተገን ጠይቀው መኖር በጀመሩባት በጀርመን የህዝብ እንደራሴ የሆኑት የኮንጎው ተወላጅ ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ማንነታቸውንና እንዴት ፖለቲከኛ ለመሆን እንደበቁ ያስቃኘናል ።
ብሬመን በሰሜን ምዕራብ ጀርመን የምትገኝ የንግድና የኢንዱስትሪ ከተማ ናት ። በህዝብ ብዛት ከሰሜን ጀርመን ግዛቶች ሁለተኛውን ደረጃ ላይ ስትገኝ ከጀርመን ደግሞ 10 ኛ ቦታን ትይዛለች ። ከሰኔ 2004 አም አንስቶ ኤሎምቦ ቦላዬላ የክፍለ ግዛትነት ደረጃ ያላት የብሬመን ከተማ ምክር ቤት   አባል ናቸው ። የ27 አመት ወጣት ሳሉ ነበር ከትውልድ ሃገራቸው ኮንጎ በያኔው አጠራሯ ከዛየር ወደ ጀርመን የተሰደዱት ። ጀርመን የመጡትም እጎአ በ1992 ነው ። ያኔ ተገን ጥየቃ ጀርመን የገቡት ቦላዬላ ከዛሬ 13 አመት አንስቶ የህንፃ ግንባታ መሣሪዎች መደብር የሽያጭ ክፍል ውስጥ ነው የሚሰሩት ። በጀርመን ከውጭ ዜጎች በእጅጉ የሚጠበቀውን ከህብረተሰቡ ጋር ተመሳስሎና ተቀራርቦ መኖርን ተግባራዊ አድርገው የብሬመን ፌደራዊ ክፍለ ሃገር ምክር ቤት አባል እስከ መሆን የደረሱት ቦላዬላ አሁንም የቀድሞው ሥራቸውን አልተዉም ።  ወደ መደብሩ ጎራ ያለ አያጣቸውም ። ሰዉ ሁሉ ያውቃቸዋል ፤
ያደንቃቸዋልም ። ቦሎዮላ በተወከሉበት በብሬመን ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በጀርመን የምክር ቤት መቀመጫ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ጀርመናዊ ናቸው ። ቦሎዮላ በጀርመን ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እሆናለው ብለው አልመውም አያውቁም ። ፓርቲያቸው ሶሻል ዲሞክራት በብሬመን ፌደራዊ ክፍለ ሃገር ለውድድር ካቀረባቸው ሰዎች ውስጥ የርሳቸው ስም ወደ ኋላ የሰፈረ ቢሆንም የብሬመን ህዝብ  ስለፈለጋቸው መርጧቸዋል ። በቀጥታው ድምፅ አሰጣጥ ጥሩ ውጤት ካመጡት 6 የፓርቲያቸው እጩ ተወዳዳሪዎች አንዱ ለመሆን ቻሉ ።  ቦሎዮላ እንደሚሉት ለዚህ ያበቃቸው ከሰዎች ጋር ያላቸው መልካም ግንኙነት ነው ።   

« ከህዝቡ ጋር ጥሩ ተሞክሮ አለኝ ። ህዝቡ ፣ ስለ እኔ በጎ አመለካከት ነው ያለው ። ምናልባት ይሄ ደግሞ « ሁሉም ሰዎች ጥሩ ናቸው በሚለው  በኔ አመለካከት ምክንያት ሊሆን ይችላል ። ያንንም አሳያለሁ ። መናገር የምችለው ከሞላ ጎደል አዎንታዊ ይዘት ያላቸው መሆናቸውን ነው   ።  »

የኮንጎው ተወላጅ ቦሎዮላ የህዝብ እንደራሴ ቢሆኑም አጀማመራቸው ግን ቀላል አልነበረም ። የትውልድ ሃገራቸውን ዛየር የአሁኗ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክን ከዛሬ 20 አመት በፊት ለቀው የወጡት ያለ ምክንያት አይደለም ። ያኔ በሥልጣን ላይ የነበሩት አምባገነኑ ሞቡቱ ሴሴሴኮ ለሃገሪቱ የረባ ነገር ባለመሥራት ኤኮኖሚዋን በማንኮታኮት የህዝቡ የኑሮ ደረጃ እንዲያሽቆለቁል በማድረግ ስማቸው የሚነሳ መሪ ነበሩ ። ቦሎዮላ እጎአ በ1990 የሞቡቱ ሴሴኮን አገዛዝ በመቃወም ይካሄድ በነበረው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተሳታፊ ነበሩ ። በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉ ምክንያት የሆናቸውም ተማሪ ሳሉ ከመምህራቸው ያገኙት ማብራሪያ ነበር ። ከመካከላችን
« ተማሪ ሳለሁ እጎአ በ1991 ነበር ዲሞክራሲ የሚለው ቃል መኖሩን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት ። ያኔም መምህሬን ምን ማለት ነው ብዮ ጠየቅኋቸው ። እርሳቸውም አንድን አገር የሚያሳድግ ጥሩ የፖለቲካ ስርዓት ማለት እንደሆነ ፤ እያንዳንዳችን ሚኒስትር ወይም መምህር የመሆን እድል እንዳለን ፣ ተጨማሪ መንገዶች ሊሰሩልን እንደሚችሉ በግልፅ ነገሩኝ ። »
ይህ ገለፃም የወጣቱን የቦሎዮላ ልብ አነሳሳ ።እጎአ የካቲት 16 ፣ 1992 እሁድ እለት በሺህዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ሞቦቱን በመቃወም ሰልፍ ወጡ ። የታቀደው ሠላማዊ ሰልፍ እንደመሆኑ ህዝቡ ሲዘምር በዋና ከተማይቱ ኪንሻሳም ዝማሬው ያስተጋባ እንደነበር ቦሎዮላ ያስታውሳሉ ። ሆኖም የሰልፉ መጨረሻ አላማረም ። ደም ፈሰሰ ። ወታደሮች ተኩስ ከፍተው ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ ሰልፈኞች ተገደሉ ። ቦሎልያም ተተኩሶባቸው ቆሰሉ ። በቀናት ውስጥ ሃገራቸውን ጥለው ሸሹ ። በሞስኮ በኩል አድርገው ጀርመን ገቡ ። ግን ጀርመን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም ። የመጀመሪያዎቹን አመታት ከዛሬ ነገ ወደ ሃገሬ እባረራለሁ ከሚል ስጋት ጋር ነበር ያሳለፉት ጀርመን የመቆየት መብታቸውን ለማስከበር 5 አመታት ወሰዶባቸዋል ። ጀርመን የመኖር ፈቃድ እስኪያገኙ ድረስ አንዳንዴ ማመልከቻቸው ተቀባይነት ሲያጣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመቆያ ፈቃዳቸው እንደገና ሲራዘምላቸው ነው የቆዩት ። የ 3 ሺህ መራጭ ድምፅ አግኝተው ተመረጡ   
በተወሳሰቡ መንገዶች ከሃገር የወጡት ቦሎዮላ በመጨረሻ ጀርመን ገቡ ። እንደ ተገን ጠያቂ ጀርመን የመቆየት መብታቸውን ለማስከበር ለአመታት ታግለዋል ። ከጎናቸው የቆመው ህዝብ ፣ በቤተክርስቲያንና በቤተክርስቲያን መዝምራን ቡድን ውስጥ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጀርመን እንዲቆዩ ምክንያት እንደሆናቸው ይናገራሉ ።
አትሞ ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,   
በትውልድ ኮንጎዋዊው ቦሎዮላ የመዘምራኑን ቡድን አቋቁመው በፖለቲካውም መሳተፍ ጀመሩ ። የውጭ ዜጋ ለሆኑ ተማሪዎች የተሻለ እድል የሚሰጥ ህግ እንዲወጣ ያቀረቡት  ሃሳብ በብሬመን ፌደራዊ ምክር ቤት በሚገኙ የሥራ ባልደረቦቻቸው ዘንድ አድናቆት አትርፎላቸዋል ። በብሬመን የ ፓርቲያቸው የ SPD ፖለቲከኞች ያመሰግኗቸዋል ። በብሬመን ፌደራዊ ምክር ቤት የጀርመን ሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ ሊቀመንበር ብዮርን ሸፐ ስለ ቦሎዮላ  በጎ አስተያየት ነው ያላቸው  ።
« የተለያዩ ሰዎች የሚገኙበት ቡድን ነው ። የተለያየ መነሻ ያላቸው ሰዎች ከሚገኙበት ቡድን ውስጥ ቦሎዮላ ቦታቸውን አግኝተዋል ። በመካከሉም የቡድኑ ሙሉ አባል ሆነዋል ። እስካሁን ሁሉም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ። »

ሞቡቱ ከሞቱ 15 አመታት ተቆጥረዋል ። ሃገሪቱም የህግ መንግሥታዊ ዴሞክራሲ መስመር ለመከተል እየሞከረች ነው ። ቦሎዮላም ካሉበት ከጀርመን የኮንጎን ሁኔታ ይከታተላሉ ። ህዝባቸው ምን ያህል ለአመታት በፖለቲከኞች ጭቆና ሥር እንደቆዩና የመንግሥት ባለሥልጣናትም አለአግባብ ሥልጣናቸውን ይጠቀሙ እንደነበር ታዝበዋል ። በቦሎዮላ እምነት ዲሞክራሲም ሆነ ፖለቲካ በቅጡ ሊጤን ይገባል ።
« ዲሞክራሲ ጨዋታ አይደለም ። ፖለቲካ ምኞት አይደለም ፤ እውነታውን መጋፈጥ እንጂ ።አማራጮችን ማወቅ ያስፈልጋል ፤ ገላጋይ ሃሳቦችንም ማመር እንዲሁ ። »
በኮንጎ ለውጥ ማምጣት ቦሎዮላ ለጊዜው ትኩረት የሰጡት ጉዳይ አይደለም ። ያ ከአሁን ወዲያ የርሳቸው አለም ሊሆን አይችልም ። ሆኖም ይላሉ የተወለዱበት የኖሩበት ሃገር መሄዳቸው አይቀርም ።  የ SPD ው ፖለቲከኛ ቦሎዮላ ሲክ በተባለችው ከተማ የአናፂነት ሙያ ትምሕርት አጠናቀዋል ። ትምህርታቸውን ባጠናቀቁ በአመቱ በአንድ የግንባታ መሣሪዎች መደብር ውስጥ መሥራት ጀመረ ። እዚያ ሳሉም የሠራተኞች ማህበር ውስጥ ከ 2003 ጀምሮ በትጋት ሲሳተፉፍ ከቆየ በኋላ በ2009 የሠራተኞች ማህበር ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ ። በዚህ ጊዜም የኦዝለብስሃውዘን ከተማ የአንድ አካባቢ የ SPD ማህበር አባል ሆኑ ። በ 2011 የክፍለ ግዛትነት ደረጃ ላላት የብሬመን ከተማ ምክር ቤት አባልነት ከ41 እጩዎች ጋር ተወዳድረው በምክርቤቱ መቀመጫ ለመያዝ  በቁ ። አሁን በምክር ቤቱ የውጭ ተወላጆች ከጀርመን ህብረተሰብ ጋር ተመሳስለው የሚኖሩበትን ጉዳይ የሚከታተል ፣ የፌደራልና የአውሮፓ ጉዳዮች አለም አቀፍ ግንኙነት የልማት ትብብር ኮሚቴ ተወካይ ናቸው ,።
ሳሙኤል ቦሎዮላ በተባለው የሙዚቃ ስማቸወ የሚታወቁት ቦላዮላ በትርፍ ጊዜያቸው ከበሮ ይመታሉ ። እጎአ በ 2002 አም በመሰረቱት ድንበር አልባ በተባለው የመዘምራን ጓድ ውስጥም ይሳተፋሉ ።
ኤሎምቦ ቦላዬላ «ለጊዜው መቆም ተቀባይነት ይኖረዋል ሆኖም እስከ ለዘላለሙ መቀመጥ ግን ሐጢአት ነው» ይላሉ ።  በጀርመን የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ተመሳስለው ለመኖር ፣ ሥራ አጥ ላለመሆን ፣ አድልኦንም ለመከላከልና የተሻለ የትምህርት እድል ለማግኘት የውሳኔ ሰጭ አካል መሆን ነው የተሻለው አማራጭ ። ርሳቸው እንደሚሉት ከውጭ ሆኖ ለውጥ የማምጣቱ እድል ዝቅተኛ ነው ። የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በቦላዬላ እምነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ከሆኑ ብቻ ነው ። ስለዚህ ይላሉ ቦላዬላ ሰዎች በፖለቲካ እንዲሳተፉ ማበረታት ይገባል ።  ቦላዬላ እጎአ ታህሳስ 28 ፣ 1965 ኮንጎ መዲና ኪንሻሳ ነው የተወለዱት ። አባታቸው የወንጌላዊያን ቤተክርስቲያን ሰባኪ ናቸው ። በ1998 ካገቧቸው ከባለቤታቸው አንጌላ ቦላዬላ ማርክዋርት 5 ልጆች አፍርተዋል። 

Der Bremer Abgeordnete Elombo Bolayela vor der Bremischen Bürgerschaft (Landtag). Er ist ein Migrant aus der Demokratischen Republik Kongo und 2011 für die SPD als erster afrikanischstämmiger Abgeordneter in einen deutschen Landtag eingezogen. Foto DW/Philipp Sandner, 2012 in Bremen
ምስል DW

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ