1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከበጎ ፈቃደኛ ልዩነህ ታምራት ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011

ልዩነህ ታምራት ወጣቶችን በዘላቂነት ከጎዳና ሕይወት ለማላቀቅ ሥነ-ልቦናዊ እገዛ፣ ፍቅር እና የክኅሎት ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል የሚል እምነት ያለው በጎ ፈቃደኛ ነው። ልዩነህ ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር በመተባበር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አራት የማገገሚያ ማዕከላት የማቋቋም ውጥን ጭምር አለው። 

https://p.dw.com/p/3MLX1
Afrika Obdachlosigkeit  - Straßenkinder schlafen auf einer Fussgaengerbruecke in Addis Abeba
ምስል Imago/photothek

ከበጎ ፈቃደኛ ልዩነህ ታምራት ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ

በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ፣ ብሔራዊ፣ መርካቶ እና ፒያሳን ጨምሮ በርካታ ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ታዳጊዎች እና ወጣቶች መመልከት የተለመደ ሆኗል። በጉዳዩ ላይ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በምጣኔ-ሐብታዊ፤ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፈተናዎች ምክንያት ዜጎች ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ፍልሰት መጨመሩ ችግሩን ውስብስብ አድርጎታል።

ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ታዳጊዎችን እና ወጣቶችን ለመርዳት ገፋ ሲልም በዘላቂነት ለማቋቋም ግለሰቦች እና የግብረ ሰናይ ተቋማት የተለያዩ ጥረቶች ያደርጋሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ ልዩነህ ታምራት ነው። ልዩነህ ታምራት ተወልዶ ያደገው በሐዋሳ ከተማ ቢሆንም ኑሮውን በአዲስ አበባ ካደረገ ዓመታት ተቆጥረዋል። ረዥም ጊዜውን በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ያሳልፍ እንጂ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካውንቲንግ እና ፋይናንስ አጥንቷል። በበጎ ፈቃድ ሥራ ላይ የተሰማራው ታምራት የዛሬ የወጣቶች መድረክ እንግዳችን ነው። 

ሙሉ መሰናዶውን የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ