ከባድ የመሪት መንቀጥቀጥ በደቡባዊ እስያ
ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2008ማስታወቂያ
በሰሜን ምሥራቅ አፍጋኒስታን በተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቢያንስ 150 ሰዎች ሞታቸዉ ነዉ የተዘገበዉ። በሰሜን ፓኪስታን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የአፍጋኒስታን የታክሀር ግዛት የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስከ ሕንድ ኒው ዴሊ ከተማ ድረስ መሰማቱን የሕንድ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ተያይዞ የወጣው ዜና አመልክቶዋል። በአካባቢው ተማሪዎች ከአደጋው ለማምለጥ ከትምህርት ቤታቸውን ሲውጡ በተፈጠረው ግፊያ እና ጭንቅንቅ ወቅት ቢያንስ 12 ልጃገረዶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ