1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ከ35 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ቀያቸው ተመለሱ ተባለ 

ቅዳሜ፣ የካቲት 30 2011

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ-መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ገለጹ። አቶ አሻድሊ ከክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎች በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል እንደሚገኙ ለDW ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3EiwV
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተጠለሉ ተፈናቃዮች ይቀራሉ

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ-መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ገለጹ። አቶ አሻድሊ ከክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎች በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል እንደሚገኙ ለDW ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተቀስቅሶ በነበረው ግጭት የተፈናቀሉ ከ35 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የምዕራብ ኢትዮጵያ የጸጥታ ዕዝ አስታወቆ ነበር። የአካባቢውን የጸጥታ ኹኔታ ለመቆጣጠር የተቋቋመው ዕዝ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች መከፈታቸውን ተቋርጠው የነበሩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች መጀመራቸውን አስታውቋል።  ነጋሳ ደሳለኝ ከአሶሳ ተጨማሪ ዘገባ አለው። 
ነጋሳ ደሳለኝ
እሸቴ በቀለ