1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከቦሩስያ ዶርትሙንዱ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው በቁጥጥር ስር ዋለ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 4 2009

የጀርመኑን ቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ቡድን አባላትን ይዞ ይጓዝ በነበረ አውቶቡስ ላይ ትናንት ምሽት ስለ ደረሰው ፍንዳታ የጀርመን  ፌዴራል አቃቤ ሕግ  ምርመራ ጀመረ። የቦሩስያ ዶርትሙንድ ቡድን ተጫዋቾች ከፈረንሣዩ ሞናኮ ጋር ለነበረው የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥማያ በአውቶቡስ ወደ ሜዳው በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ፍንዳታው የደረሰው።

https://p.dw.com/p/2b9B4
Borussia Dortmund Teambus nach Explosionen
ምስል picture-alliance/AP Images/M. Meissner

የጀርመኑን ቦሩስያ ዶርትሙንድ የእግር ኳስ ቡድን አባላትን ይዞ ይጓዝ በነበረ አውቶቡስ ላይ ትናንት ምሽት ስለ ደረሰው ፍንዳታ የጀርመን  ፌዴራል አቃቤ ሕግ  ምርመራ ጀመረ። የቦሩስያ ዶርትሙንድ ቡድን ተጫዋቾች ከፈረንሣዩ ሞናኮ ጋር ለነበረው የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥማያ በአውቶቡስ ወደ ሜዳው በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ፍንዳታው የደረሰው።

ከምሽቱ አንድ ሰአት ከሩብ ሲል ከተከረከመ የተክል አጥር ጥግ ላይ በደረሰው ሦስት ተከታታይ ፍንዳታ ተጨዋቾቹን ጭኖ የነበረው አውቶቡስ መስኮት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። እንዲያም ኾኖ   አንድ ተጨዋች ብቻ ከመስተዋት ስብርባሪ ፍንጣሪ እጁ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጪ ሌሎች ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጧል።  ፈንጂው የብረት ቁጥርጥራጮች እንደነበሩበት ተገልጧል። የዶርትሙንድ ፖሊስ ፕሬዚደንት ግሬጎር ላንገ ጥቃቱ በአውቶብሱ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተናግረዋል።

«መጀመሪያውኑም እንደገመትነው አሁንም ቢሆን ጥቃቱ የተቃጣው በቦሩስያ ዶርትሙንድ አውቶቡስ ላይ ኾን ተብሎ ነው ባይ ነን። በአሁኑ ሰአት ግን ጥቃቱ በእርግጥም የደረሰበትን ምክንያት መናገር አንችልም። እናም ከመጀመሪያው አንስቶ ሊሆኑ ይችላሉ የምንችላቸውን ነገሮች በሙሉ በማጤን ሁኔታው በእርግጥም ከባድ በመሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ አጸፌታ ማድረግ ነበረብን።»

Deutschland Dortmund vor dem Spiel
ምስል picture alliance/AP Photo/M. Meissner

ፖሊስ በፍንዳታው ጠርጥሮ የያዘውን ግለሰብ ለማሠር የእስር ማዘዣ ጠይቋል። በፍንዳታው ቦታ የተገኘ ደብዳቤ ጥቃቱ የደረሰው በእስልምና አክራሪ ቡድኖች ሳይሆን እንደማይቀር ጠቁሟል ተብሏል። የቦሩስያ ዶርትሙንድ ቡድን ኃላፊ  ሐንስ ዮአሒም ቫትስከ ቡድናቸው ድንጋጤ ቢደርስበትም የታቀደው ጨዋታ ዛሬ እንደሚደረግ ትናንት ተናግረዋል።

«ቡድኑ በእርግጥም ከባድ ድንጋጤ ነው የደረሰበት። ያ ግልጽ ነው። የኛ ተግባር አሁን አንዳንድ ጉዳዮችን በዝርዝር መመልከት ነው። ከዚያ 24 ሰአት ካለፈ በኋላ ነገ የግድ መጫወት አለብን። ያ የኛ ተግባር ነው።»

ቦሩስያ ዶርትሙንድ ከፈረንሳዩ አቻው ሞናኮ ጋር ለሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ግጥሚያ ዛሬ ማታ እንደሚጫወት ተዘግቧል። ተጨዋቾቹ ዛሬ ከሰአት አጠር ያለ ልምምድ አድርገዋል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ