ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ከበደ አኒሳ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:48 ደቂቃ
19.05.2019

ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ከበደ አኒሳ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

ከበደ አኒሳ ለኢትዮጵያ ሔራልድ፣ ቮይስ ኦፍ ኢትዮጵያ እንግሊዘኛ ጋዜጦች እንዲሁም ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ድምጽ የአማርኛ ጋዜጦች ለረጅም አመታት የሰሩ አንጋፋ ጋዜጠኛ ናቸው። ኢትዮጵያ ትቅደም የተባለውን መፈክር ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት እሳቸው እንደነበሩ ያስታውሳሉ።

የዛሬው የመዝናኛ መሰናዶ እንግዳ አንጋፋው ጋዜጠኛ ከበደ አኒሳ ናቸው። አቶ ከበደ የኢትዮጵያ ሔራልድ፣ ቮይስ ኦፍ ኢትዮጵያ እንግሊዘኛ ጋዜጦች እንዲሁም ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ድምጽ የአማርኛ ጋዜጦች ለረጅም አመታት የሰሩ አንጋፋ ጋዜጠኛ ናቸው። ኢትዮጵያ ትቅደም የተባለውን መፈክር ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት እሳቸው እንደነበሩ ያስታውሳሉ። በዚህም ምክንያት በወቅቱ ሥልጣን ላይ በነበሩት በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ማብራሪያ ተጠይቀዋል። አቶ ከበደ አኒሳ በጋዜጠኝነት ሙያቸው ጳውሎስ ኞኞ፣ ነጋሽ ገብረማርያም፤ ሙሉጌታ ሉሌ፤ ማዕረጉ በዛብህን ከመሳሰሉ አንጋፋዎች ጋር ሰርተዋል። ሥራቸው ከንጉሳዊው ሥርዓተ መንግሥት ጀምሮ ወታደራዊውን የደርግ ሥርዓት ተሻግሮ ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ እስከቆየባቸው ጊዜያት የዘለቀ ነው።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ
 

ተከታተሉን