1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ ጋር የተደረገውን  ቃለ-መጠይቅ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 12 2013

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ማስጠንቀቂያ አለመስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ አረጋገጡ። ዋና ዳይሬክተሩ በዶይቼ ቬለ ዘገባዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሉት ያሏቸውን ቅሬታዎች ግን በዝርዝር አስረድተዋል።

https://p.dw.com/p/3lezO
Äthiopien l Teilnehmer einer Konferenz für Pressefreiheit
ምስል DW/Y. Gebregziabher

ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ማስጠንቀቂያ አለመስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ አረጋገጡ። ዋና ዳይሬክተሩ በዶይቼ ቬለ ዘገባዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሉት ያሏቸውን ቅሬታዎች ግን በዝርዝር አስረድተዋል።

ባለሥልጣኑ የሬውተርስ የአዲስ አበባ ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ፤ ለዶይቼ ቬለ እና ለቢቢሲ ራዲዮ ጣቢያዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ የሚል መረጃ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሰራጭቶ ነበር። መረጃው የተሰራጨው የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ለሸገር ራዲዮ ጣቢያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ መሠረት በማድረግ ነው።

"ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው ማስጠንቀቀያ የለም። ምን አልባት ቢሯችን ጠርተን ያደረግንው ምክክር እንደዚያ ተደርጎ ተገልጾ ከነበረ ስህተት ነው። የጽሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር ግን ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው የለም" ያሉት ዶክተር ጌታቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በዘገባዎች ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት አስረድተዋል።

"ወደ አንድ ወገን ማጋደላችሁ ይኼ ነው ሊባል የሚችል አይደለም። በብዙ ቅሬታ አቅራቢዎች ጭምር የተደገፈ ነው። እኛም ደግሞ በሙያዊ ትንታኔ ያንን አይተን ያንን ቅሬታችንን የምናቀርብ ይሆናል። በዚህ አይነት ከቀጠለ ሌሎቹን ተጠያቂ እንዳደረግንው ሁሉ ዶይቼ ቬለ በዚያ መልኩ አይጠየቅም ማለት አይቻልም" ሲሉ ተቋማቸው ያለውን ቅሬታ ዶክተር ጌታቸው አስረድተዋል።

ዶይቼ ቬለ ለማንም የማይወግን ዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛ ነው። በኢትዮጵያ በሚሰራቸው ዘገባዎች ከቀበሌ እስከ ፌድራል መንግሥት ያሉ ባለሥልጣናትን ያነጋግራል። የመረጃዎችን ትክክለኛነት የመንግሥት የመረጃ ምንጮችን ጨምሮ ከተለያዩ ወገኖች የጋዜጠኝነት መርኅ በሚያዘው መሠረት ያጣራል። የተለያዩ ሐሳቦችንም ያስተናግዳል። 

ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ድንቁ ጋር የተደረገውን  ቃለ-መጠይቅ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ