ከኢትዮጵያ የተባረረችው ጋዜጠኛ16 ሰኔ 2002ረቡዕ፣ ሰኔ 16 2002ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ እንድትወጣ የተደረገችው የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጋዜጠኛ አንዳችም ጥፋት እንዳልፈፀመች አስታወቀች ። የምርጫ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ዜናዎችን ለመዘገብ ከምርጫው ቀደም ብላ ኢትዮጵያ የገባችው ጋዜጠኛ ሂተር ሞርዶክ ለዶይቼቬለ እንደተናገረችው ለስራዋ አስፈላጊ የሆኑ ፈቃዶችን አግኝታለች ።https://p.dw.com/p/O0dGምስል DWማስታወቂያሆኖም ዘገባ ለማጠናቀር ወደ ሐረር በሄደችበት አጋጣሚ በአካባቢው ግጭት ስለመኖሩ የሰማችውን መረጃ ካጣራች በኃላ በፖሊስ ተይዛ ሰኔ 10 ,2002 ዓም ከኢትዮጵያ መባረሯን አስታውቃለች ። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን አበበ ፈለቀ ካይሮ ግብፅ የምትገኘዋን ጋዜጠኛ ሞርዶክን በስልክ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ። አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ