1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከእንግዲህ የልብ ህሙማንን በአገር ዉስጥ ማከም ይቻላል

ማክሰኞ፣ የካቲት 10 2001

የዛሬ 30ዓመት አንድ የልብ ህመምተኛ ህፃን ከባህር ማዶ አሻግሮ ማሳከም ብርቅ ነበር። ዛሬ ግን አንድ ህፃን ብቻ ሳይሆን በቀን ከአምስት የሚልቁ ህመምተኞችን አስተኝቶ ደረጃዉን የጠበቀ ህክምና መስጠት የሚያስችለዉ የልብ ህሙማን ሊረዱበት የሚችሉበት ሃኪም ቤት አገር ዉስጥ ተገንብቶ ስራዉን ጀመረ።

https://p.dw.com/p/GwAq
...ልብ ቀጥ ካለ...
...ልብ ቀጥ ካለ...ምስል AP

ይህ ብስራት የተማዉ ባለፈዉ ሳምንት ነዉ። ሃኪም ቤቱ በበጎ አድራጊዎች ርብርብ ተገንብቶ ስራ መጀመሩ በስራዉ ለተሳተፉ ታታሪዎች ብቻ ሳይሆን ዜናዉን ለሚሰሙት ሁሉ አመርቂነቱ አያነጋግርም። የሃኪም ቤቱ አገልግሎት እንዳጀማመሩ ለህፃናት ብቻ ሳይሆን አዋቂዎችንም ያካትታል። በቀጣይም የምርምር ማዕከል የሚገነባ ሲሆን ባለሙያዎችን ማሰልጠንኑም በተጓዳኝ ይከወናል።