1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኮፐንሄገን ጥቂትና ምንም...

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2002

ከኮፐንሄገኑ ጉባኤ ቅዳሜ ዕለት ተገኘ የሚባለዉ ስምምነት እንደዉም በተመድ ታሪክ ኢዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተከወነ ነዉ የሚል ክስ ቀርቦበታል።

https://p.dw.com/p/LAu4
...ጬኸቴን ብትሰሙኝ....ምስል AP

ስምምነቱ የተደረገዉ ድሃዎቹን አባል አገራት ባገለለ መልኩ ነዉ የሚሉት ዘገባዎች የድርድሩ ተዋናዮች ዩናይትድ ስቴትስ፤ ቻይና፤ ህንድ፤ ብራዚል፤ ደቡብ አፍሪቃ፤ እንዲሁም የአዉሮጳ አገራት መሪዎች መሆናቸዉን ይዘረዝራሉ። እናም የተጠቀሱት አገራት በዝግ ከተስማሙባቸዉ ነጥቦች መካከል የዓለም የሙቀት መጠን ከ2ዲግሪ ሴልሲየስ እንዳይበጥ የሚለዉ ሲኖር እዚያ ግብ ጋ ለመድረስ ለዚህ መዘዝ የዳረጉት የበካይ ጋዞች ልቀት እያንዳንዳቸዉ በምን ያህል መጠንን ለመቀነስ ዝግጁ እንደሆኑ የተወራ ነገር የለም። በበጋ በሰደድ እሳት፤ በማዕበልና ጎርፍ፤ በክረምቱም እንዲሁ በከባድ በረዶና ቁር የሚጠቁት ሆኖም በደህና ቀን ባበለፀጉት የምጣኔ ሃብታቸዉ አማካኝነት ገበናቸዉ ተከድኖ የሚኖሩት በርካታ ሃብታም አገራት ብክለቱን ለመቀነስ በሚወሰደዉ ርምጃ ግንባር ቀደም አልሆኑም። ይልቁንም የኢንዱስትሪዉ አብዮት የጣለዉ ጠባሳ ተዘንግቶ ዛሬ ለእድገት የሚቻኮሎ የያኔ ድሃ አገራት ከመሸ የአየር ጠባይ ለዉጥ ተጠያቂ ተደርገዉ ሲቀርቡ ተስተዉሏል። በኮፐንሃገኑ ጉባኤ አልቦ ዉጤት መጠናቀቅ ብሪታኒያ ቻይናን ተጠያቂ አድርጋለች። ለማንኛዉም ከጉባኤዉ ጥቂት ተገኛ እና አረ ምንም የሚሉት በርክተዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ