ከዉጭ መልስ ንግድ
ሰኞ፣ ጥር 26 2006ማስታወቂያ
የሄዱበት ሀገር አዲስ ባህልና አኗኗር የህይወት አቅጣጫቸዉን በበጎ የቀየረላቸዉ የመኖራቸዉን ያህል፤ ያልጠበቁት የገጠማቸዉ፤ ያም ከማይላቀቁት አዙሪት ከቶ፤ ቆይ ዘንድሮ፤ ቆይ የሚመጣዉ ዓመት እያሉ ጥሪት ለመቋጠር ሲዋትቱ ዓመት ዓመትን እያፈራረቀ፤ እነሱም ወደተመኙት ሳይደርሱ ጊዜዉ የነጎደባቸዉ ጥቂት አይደሉም። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ ከእነዚህ ይለያሉ፤ ከሄድኩበት ሀገር ገንዘብ ቢቀር ጠንካራ የሥራ መንፈስን ሰንቄ በመመለስ የራሴን እንቅስቃሴ ጀምሬያለሁ ባይ ናቸዉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ