1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከውሃን ቻይና አዉጡን የሚሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ጨምሯል

ቅዳሜ፣ ጥር 30 2012

በዉሃን ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመጓጓዣ ወጪያቸውን ራሳቸው ሸፍነው ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ተብሏል። ተማሪዎቹ ይህን ለማድረግ ግን አሁንም የሀገራቸው ትብብር እንደሚስፈልጋቸዉ እየገለፁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3XPWY
Frankreich fliegt Staatsbürger aus Wuhan aus
ምስል Getty Images/AFP/H. Retamal

መመለስ የሚሹት ተማሪዎት ጉዳይ

በቻይና ውሃን ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች መካከል 95 በመቶ ያህሉ ወደ ሀገሩ መመለስ እንደሚፈልግ ተገለፀ። ይህ የታወቀዉ ዶይቼ ቬለ በቻይና ውሃን ከተማ ከሚገኘው የኢትዮጵያውን ተማሪዎች ህብረት ጋር ባካሄደዉ ቃለ-ምልልስ ነዉ። በዉሃን ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመጓጓዣ ወጪያቸውን ራሳቸው ሸፍነው ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ተብሏል። ተማሪዎቹ ይህን ለማድረግ ግን አሁንም የሀገራቸው ትብብር እንደሚስፈልጋቸዉ እየገለፁ ነዉ። ተማሪዎቹ አስፈላጊውን የመውጫ ፍቃድ መንግሥታቸው እንዲያመቻችቸው ይሻሉ።  በሌላ በኩል ተማሪዎቹ ከሚኖሩበት ቤት መውጣት እና ከሰው ጋር መገናኘት አለመቻላቸው ሌላው ጭንቀታቸዉ መሆኑም ታዉቋል። በኮሮና ቫይረስ መያዝ ስጋት ውስጥ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች አስመልክቶ፤ ልደት አበበ ከተማሪዎቹ ህብረት ሊቀመንበር ከዘሀራ አብዱልሀዲ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጋለች። 

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ